በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይበልጥ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲመሩ እየረዳቸው ነው

ይበልጥ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲመሩ እየረዳቸው ነው

ይበልጥ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲመሩ እየረዳቸው ነው

“መጥተህ ተከታዬ ሁን” (እንግሊዝኛ) የተሰኘው መጽሐፍ ባነበቡት ሰዎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። አንዲት ሴት “ኢየሱስ ይበልጥ እውን ሆኖልኛል” ስትል ተናግራለች። አክላም እንዲህ ብላለች፦ “ኢየሱስ የሚጫወተውን ሚና በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ አግኝቻለሁ። አሁን የበለጠ ትርጉም ያለው ሕይወት መምራትና ለሰው ልጅ በእጅጉ የሚያስፈልገውን ምሥራች በመስበኩ ሥራ መካፈል እፈልጋለሁ።”

አንድ አባት እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ይህ መጽሐፍ ኢየሱስ የተወልንን ፍጹም ምሳሌ መከተል ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን እንድገነዘብ አስችሎኛል። . . . ይህ መጽሐፍ ኢየሱስ ምድር ሳለ በሰጣቸው ትምህርቶች እንዲሁም እንደ ትሕትና፣ ፍቅር፣ ከፍተኛ ትዕግሥት፣ ታዛዥነትና ጽናት ባሉ ባሕርያቱ ላይ ማሰላሰል እንዳለብኝ አስተምሮኛል። ኢየሱስ በዚሁ እንድቀጥል የሚያበረታታ ግሩም ምሳሌ ትቷል።”

ሌላ አንባቢ ደግሞ በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ካለው ሐሳብ ጋር ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልጿል። ሐሳቡ በከፊል እንዲህ ይላል፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ የተሾመ መሪ ነው፤ እያንዳንዱ ሰው የሚያስፈልገው እንዲህ ያለ መሪ ነው። . . . ይህ መጽሐፍ ኢየሱስን ይበልጥ በቅርበት እንድታውቀውና ከምንጊዜውም በላይ ፈለጉን እንድትከተል ይረዳሃል።” ከዚያም አንባቢው “በእርግጥም መጽሐፉ ኢየሱስን እንድንወደውና እንድናምንበት ብሎም እንድንታዘዘውና እንድንከተለው ይረዳናል” ሲል አክሎ ተናግሯል።

“መጥተህ ተከታዬ ሁን” የተባለው መጽሐፍ 192 ገጽ ያለው ሲሆን ኢየሱስ በምድር ሳለ ያሳለፋቸውን አንዳንድ ነገሮች የሚያሳዩ 13 ባለ ሙሉ ገጽ ውብ ሥዕሎች አሉት። ይህ መጽሐፍ እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።