በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

በመጀመሪያ ማቴዎስ 25:1-12ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

4. ․․․․․

ለውይይት፦ አምስቱ ልጃገረዶች ዘይታቸውን ለሌሎቹ ማካፈል ያልፈለጉት ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 25:8, 9ን አንብብ።

ያለንን ነገር ለሌሎች ማካፈላችን ተገቢ የሚሆነው መቼ ነው? ተገቢ የማይሆነውስ በምን ጊዜ ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 6 ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ የማን ነው? መዝሙር 24:․․․

ገጽ 9 የተጠማ ሁሉ ምን ነገር መውሰድ ይችላል? ራእይ 22:․․․

ገጽ 18 አስተዋይ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው? ምሳሌ 17:․․․

ገጽ 29 ሰው የራሱ ተላላነት ምን ሊያደርገው ይችላል? ምሳሌ 19:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ስለ ነቢያት ምን የምታውቀው ነገር አለ?

5. ․․․․․

ንጉሥ ኢዮአቄም እንዳይዘው ሸሽቶ ያመለጠው ነቢይ ማን ነው?

ፍንጭ፦ ኤርምያስ 26:17-23ን አንብብ።

6. ․․․․․

ኢየሩሳሌም “የፍርስራሽ ክምር” እንደምትሆን በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት የተናገረው ማን ነው?

ፍንጭ፦ ኤርምያስ 26:18ን አንብብ።

ለውይይት፦

ስለ እነዚህ ሁለት ነቢያት ካነበብክ በኋላ ስለ አምላክ ለሌሎች ለመናገር መፍራት የማይገባህ ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 29:25ን አንብብ።

▪ መልሶቹ በገጽ 21 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ሙሽሪት በዘገባው ውስጥ አልተጠቀሰችም።

2. ወደ ድግሱ የገቡት አምስቱ ልጃገረዶች ነበሩ።

3. አምስቱ ልጃገረዶች መብራትና በዕቃቸው ዘይት ይዘው የነበረ ሲሆን ሌሎቹ ልጃገረዶች ግን የያዙት መብራት ብቻ ነበር።

4. ሙሽራው የሚዘጋው በር መኖር ነበረበት።

5. ኦርዮ።—ኤርምያስ 26:20

6. ሚክያስ።