በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ዑደቶች

ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ዑደቶች

ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ዑደቶች

ንዲት ከተማ ንጹሕ አየር ብታጣና ውኃ ቢቋረጥባት እንዲሁም የቆሻሻ ማስወገጃዎቿ ቢዘጉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነዋሪዎቿ ለበሽታና ለሞት ይዳረጋሉ። ፕላኔቷ ምድራችን ግን ንጹሕ አየርና ውኃ ከጠፈር ወደ ውስጥ ማስገባትም ሆነ በውስጧ ያለውን ቆሻሻ ወደ ውጭ ማስወጣት አያስፈልጋትም! ታዲያ ሕይወት የሚኖርበት የምድር ክፍል ለመኖሪያነት ተስማሚና ምቹ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? እዚህ ላይ ቀለል ባለ መንገድ የቀረቡት የውኃ፣ የካርቦን፣ የኦክስጅንና የናይትሮጂን የተፈጥሮ ዑደቶች በመኖራቸው ነው።

የውኃ ዑደት ሦስት ደረጃዎች አሉት። 1. የፀሐይ ሙቀት ውኃን በማትነን ወደ ከባቢ አየር እንዲገባ ያደርጋል። 2. የተነነው ውኃ ሲቀዘቅዝ ደመና ይፈጥራል። 3. ደመናዎች ደግሞ በዝናብ፣ በበረዶና በውሽንፍር መልክ ወደ መሬት በመውረድ ዑደቱ የተሟላ እንዲሆን ያደርጋሉ። በየዓመቱ ምን ያህል ውኃ በዚህ ዑደት ውስጥ ያልፋል? ሁሉንም የምድር ክፍል ከ100 ሴንቲ ሜትር በላይ ሊደርስ በሚችል ጥልቀት የሚሸፍን ውኃ በዚህ ዑደት እንደሚያልፍ ይገመታል።

2

← ◯

3

1

↓ ↑

→ →

የካርቦንና የኦክስጅን ዑደት ሁለት መሠረታዊ ሂደቶችን ያካትታል፤ እነሱም ፎቶሲንተሲስ እና የመተንፈስ ሥርዓት ናቸው። * ፎቶሲንተሲስ ካርቦሃይድሬትንና ኦክስጅንን ለማምረት የፀሐይ ብርሃንን፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ውኃን ይጠቀማል። በእንስሳትና በሰዎች አማካኝነት የሚካሄደው የመተንፈስ ሥርዓት ደግሞ ካርቦሃይድሬትንና ኦክስጅንን በመጠቀም ኃይልን፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ውኃን ያስገኛል። በመሆኑም የአንደኛው ዑደት ውጤት ለሌላኛው ዑደት እንደ ግባት ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሁሉ የሚከናወነው አካባቢን የሚያቆሽሽ ነገር ሳይፈጠርና ምንም የሚረብሽ ሁኔታ ሳይኖር በተቀነባበረ መንገድ ነው።

ኦክስጅን

← ←

↓ ↑

↓ ↑

↓ ↑

→ →

ካርቦን ዳይኦክሳይድ

የናይትሮጂን ዑደት ለአሚኖ አሲድ፣ ለፕሮቲን እንዲሁም ለሌሎች ኦርጋኒክ ሞለኪውልስ መፈጠር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ሀ. መብረቅና ባክቴሪያ በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን ናይትሮጂን ተክሎች ሊጠቀሙባቸው ወደሚችሏቸው ውሑዶች በሚለውጡበት ጊዜ ይህ ዑደት ይጀምራል። ለ. ተክሎች ደግሞ በበኩላቸው እነዚህን ውሑዶች በማቀላቀል ወደ ኦርጋኒክ ሞለኪውልስ ይለውጧቸዋል። በመሆኑም እነዚህን ተክሎች የሚበሉ እንስሳት ናይትሮጂን ያገኛሉ። ሐ. ተክሎችና እንስሳት በሚሞቱበት ጊዜ ደግሞ ሌሎች የባክቴሪያ ዓይነቶች የናይትሮጂንን ውሑድ በመሰባበር ናይትሮጂን ተመልሶ ወደ አፈርና ወደ ከባቢ አየር እንዲገባ ያደርጋሉ።

← ← ← ← ← ← ← ← ← ←

↓ ↑

↓ የምድር ከባቢ አየር 78 በመቶው ↑

↓ ናይትሮጂን ነው ↑

↓ ↑

↓ ↓ ኦርጋኒክ ↑

↓ ሀ ↓ ሞለኪውልስ ↑

↓ ባክቴሪያ ↓ ለ ↑ ↓ ሐ ↑

→ የናይትሮጂን ውሑዶች ባክቴሪያ →

→ → →

ፍጹም በሆነ መንገድ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል

ለምሳሌ ያህል፣ ሰዎች በቴክኖሎጂ ከፍተኛ የእድገት ደረጃ ላይ ቢደርሱም በየዓመቱ እንደገና ጥቅም ላይ የማይውሉ ብዙ ቶን የሚመዝኑ መርዛማ ቆሻሻዎችን ይጥላሉ። ምድር ግን የምታስወጣውን ቆሻሻ በሙሉ ውስብስብ የሆኑ ኬሚካላዊ ሂደቶችን በመጠቀም ቆሻሻው ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ታደርጋለች። ሃይማኖትንና ሳይንስን አስመልክተው የጻፉት ማይክል አንቶኒ ኮሪ በተፈጥሮ ላይ የሚታየው እንዲህ ያለ የተቀናጀ ዑደት “በአጋጣሚ የተከሰተ ቢሆን ኖሮ ይህ ዑደት በትክክል ራሱን እንደማይደግም በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ሆይ [“ይሖዋ ሆይ፣” NW]፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ” ብሎ ሲናገር ለሚገባው አካል ክብር መስጠቱ ነው። (መዝሙር 104:24) ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሲል ይህ ጥበቡን ለየት ባለ ባለ መንገድ ተጠቅሞበታል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.11 በአንዱ ዑደት ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር በሌላኛው ዑደት ውስጥም ሊገኝ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ ኦክስጅን በካርቦን ዳይኦክሳይድ፣ በካርቦሃይድሬትና በውኃ ውስጥ ይገኛል። በመሆኑም ኦክስጅን በካርቦንም ሆነ በውኃ ዑደት ውስጥ አለ።