በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ይህ የሆነው የት ነበር?

1. ጳውሎስ ከጢሞቴዎስ ጋር የተገናኘው የት ከተማ ነበር?

ፍንጭ፦ የሐዋርያት ሥራ 16:1-3ን አንብብ።

መልስህን በካርታው ላይ አክብብ።

ልስጥራ

ኢቆንዮን

ደርቤ

▪ የጢሞቴዎስ አባት የየት አገር ሰው ነበር? እናቱስ?

․․․․․

▪ የጢሞቴዎስ እናት ስሟ ማን ነው?

ፍንጭ፦ 2 ጢሞቴዎስ 1:5ን አንብብ።

․․․․․

▪ የጢሞቴዎስ እናት ለልጇ ምን አስተምራዋለች? ለምንስ?

ፍንጭ፦ 2 ጢሞቴዎስ 3:15ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

እንደ ጢሞቴዎስ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 ካለህ ገንዘብ ውስጥ የተወሰነውን ምን ልታደርግበት ትችላለህ? 1 ቆሮንቶስ 16:․․․

ገጽ 5 ገንዘብ ከተበደርክ ምን ትሆናለህ? ምሳሌ 22:․․․

ገጽ 11 ንጉሥ ኢዮስያስ የሐሰት አምልኮን ከይሁዳ ማስወገድ የቻለው እንዴት ነበር? 2 ዜና መዋዕል 34:․․․

ገጽ 19 ከሁሉም ሰው ጋር ጓደኛ መሆን የማይገባህ ለምንድን ነው? መዝሙር 26:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ስለ ነቢያት ምን የምታውቀው ነገር አለ?

የዮናስን መጽሐፍ አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።

2. ․․․․․

አምላክ ዮናስን የላከው ወደየትኛው ከተማ ነበር?

3. ․․․․․

ዮናስ በዚያ ከተማ ለሚኖሩ ሰዎች ምን መልእክት አስተላለፈ? ሰዎቹስ ምን ምላሽ ሰጡ?

ለውይይት፦

ዮናስ የተናደደው ለምን ነበር? መናደዱ ተገቢ ነበር? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

▪ መልሶቹ በገጽ 28 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. በትንሿ እስያ በምትገኘው በልስጥራ።

አባቱ ግሪካዊ ነበር። እናቱ ደግሞ አይሁዳዊት ነበረች።

ኤውንቄ።

‘ቅዱሳን መጻሕፍትን’ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት፤ እውነተኛ አምላክ የሆነውን ይሖዋን እንዲያመልክ ትፈልግ ስለነበር ነው።

2. ወደ ነነዌ።—ዮናስ 1:1, 2

3. በከተማይቱ ላይ አምላክ የበየነውን የጥፋት ፍርድ። ንጉሡን ጨምሮ ሕዝቡ ንስሐ ገባ።​—ዮናስ 1:2፤ 3:2-9