በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አንዲት አስተማሪ የነበራትን አመለካከት ለወጠች

አንዲት አስተማሪ የነበራትን አመለካከት ለወጠች

አንዲት አስተማሪ የነበራትን አመለካከት ለወጠች

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በጆርጂያ፣ ባቱሚ በተባለች ከተማ የምትኖር አንዲት አስተማሪ ተማሪዎቿ አሥርቱን ትእዛዛት አንድ በአንድ እንዲዘረዝሩላት ጠየቀቻቸው። ከተማሪዎቿ መካከል አና የተባለች ልጅ ሁሉንም በትክክል መዘርዘር መቻሏ አስተማሪዋን አስገረማት። ለቀረቡላት ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችም በሚያስደንቅ ሁኔታ መልስ ሰጠች። አስተማሪዋ በጣም ስለተገረመች ይህን ሁሉ ልታውቅ የቻለችው እንዴት እንደሆነ ጠየቀቻት። አናም ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናቷ ምክንያት እንደሆነ ስትገልጽላት አስተማሪዋ የአናን ንግግር በማቋረጥ የይሖዋ ምሥክሮች አክራሪዎች ናቸው የሚል አመለካከት እንደነበራት ነገረቻት።

በሌላ ጊዜ አስተማሪዋ በጆርጂያ ያለውን የኑሮ ሁኔታና አገሪቷ የገጠሟትን የተለያዩ ችግሮች አስመልክተው ጽሑፍ እንዲያዘጋጁ ለተማሪዎቹ ነገረቻቸው። አና ባዘጋጀችው ጽሑፍ መደምደሚያ ላይ የሚከተለውን ሐሳብ አስፍራ ነበር፦ “የሰው ልጆች፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያደርጉት ማንኛውም ጥረት አይሳካም፤ ምክንያቱም ኤርምያስ 10:23 እንደሚለው ‘የሰው ሕይወት በራሱ እጅ አይደለችም፤ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ አይችልም።’ ሁሉንም ችግሮች ሊያስወግድ የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው።”

በቀጣዩ ቀን አስተማሪዋ፣ አና ያዘጋጀችውን ጽሑፍ በማድነቅ ለክፍሉ ተማሪዎች የሚከተለውን አስተያየት ሰጠች፦ “አና በራሷ አባባል የጻፈችው ለየት ያለ ጽሑፍ በጣም አስደስቶኛል። የዓለም ሁኔታዎች ሊለወጡ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ በጽሑፏ ላይ ገልጻለች።” ከዚህም በተጨማሪ አስተማሪዋ በአና ጠባይ ስለተማረከች ጥሩ ሥነ ምግባሯንና ሥርዓታማ አለባበሷን በመጥቀስ በጣም እንደምታደንቃት በተማሪዎቹ ፊት ተናገረች።

አስተማሪዋ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቷ መጥተው ሲያነጋግሯት፣ ቀደም ሲል አክራሪዎች እንደሆኑ አድርጋ ታስብ የነበረ ቢሆንም አና በተባለች ተማሪዋ የተነሳ አመለካከቷን ልትለውጥ እንደቻለች ገለጸችላቸው። ይህች ሴት በ2007 የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ባከበሩበት ወቅት በበዓሉ ላይ በመገኘት ፕሮግራሙን በጥሞና ተከታተለች።

የመታሰቢያ በዓሉ ከተከበረ በኋላ አስተማሪዋ የይሖዋ ምሥክሮች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው እውቀት በጣም እንዳስደነቃት ተናገረች። በአሁኑ ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች በቋሚነት መጽሐፍ ቅዱስን እያስጠኗት ነው። እንደዚህች አስተማሪ ሁሉ አንተም አንድ መደምደሚያ ላይ ከመድረስህ በፊት ከሌሎች ሰዎች እምነትና ሥነ ምግባር በስተጀርባ ያለውን ነገር ጠለቅ ብለህ ለመመርመር እንደምትነሳሳ እናምናለን። አንድ የይሖዋ ምሥክር መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስጠናህ ለምን አትጠይቀውም?

[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አና ጽሑፍ ስታዘጋጅ