በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከዓለም አካባቢ

ከዓለም አካባቢ

ከዓለም አካባቢ

በባሕር ዳርቻዎች ላይ ሪፍ በሚሠሩ የኮራል ዝርያዎች ጤንነት ላይ የተደረገ አንድ ሰፊ ጥናት እንዳመለከተው፣ በአየር ንብረት መለወጥ ወይም በሰዎች ጣልቃ ገብነት ሳቢያ 32.8 በመቶ የሚሆኑት “ከፍተኛ የሆነ የመጥፋት አደጋ” ተጋርጦባቸዋል።—ሳይንስ፣ ዩ ኤስ ኤ

የመተንፈስ ችግር አጋጥሟቸው በአቴንስ፣ ግሪክ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የሕፃናት ክፍል ምርመራ ከተደረገላቸው ከ2,000 የሚበልጡ ልጆች ውስጥ “65 በመቶ የሚሆኑት ለዚህ ችግር የተዳረጉት አንዱ ወይም ሁለቱም ወላጆቻቸው ለሚያጨሱት የሲጃራ ጭስ በመጋለጣቸው እንደሆነ ተረጋገጠ።”—ካቲሜሪኒ—እንግሊዝኛ እትም፣ ግሪክ

“የነዳጅ ዋጋ መናር፤ የኑሮ ውድነት፤ . . . የኢኮኖሚ ውድቀት የሚፈጥረው ስጋት . . . ፤ በተደጋጋሚ የሚያጠቁን የተፈጥሮ አደጋዎች፤ በግልጽ እንደሚታየው ከእነዚህ አሳሳቢ ችግሮች ውስጥ ለአንዱም ቢሆን የአጭር ጊዜም ሆነ የረዥም ጊዜ የመፍትሔ ሐሳብ የለንም።”—ሉዊስ ማሪያ ዴ ፒዩጅ፣ የአውሮፓ አገሮች የፓርላማ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

በፖላንድ ውስጥ 17 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ልጆችና 18 በመቶ የሚሆኑት ልጃገረዶች ዕድሜያቸው 15 ዓመት ከመሙላቱ በፊት አደንዛዥ ዕፆችን ሞክረዋል።—ዝች ቫርሻቬ፣ ፖላንድ

በአንበሶችና በሰዎች መካከል ያለ ግጭት

በአፍሪካ ያለው የሕዝብ ብዛት እየጨመረ መምጣቱ የዱር አራዊት መኖሪያ እንዲቀንስ አድርጓል፤ ይህም “በተደጋጋሚ ጊዜያት ለሞት የሚያደርሱ ግጭቶች እንዲፈጠሩ” ማድረጉን አፍሪካ ጂኦግራፊክ የተሰኘው የኬፕ ታውን ጋዜጣ ዘግቧል። በተለይ አንበሶች “ሰዎችን ታዳኞቻቸው አድርገው የቆጠሯቸው ይመስላል።” ለምሳሌ ያህል፣ በታንዛኒያ አንበሶች ከ1990 ጀምሮ በየዓመቱ ቢያንስ 70 ሰው ገድለዋል። ጋዜጣው እንደዘገበው አንዳንድ ጊዜ የአንበሳ መንጎች “ሰዎችን በማጥቃት ረገድ እየተካኑ የመጡ ይመስላል፤ በጎጇቸው ደጃፍ ላይ ያገኟቸውን ሰዎች ያጠቃሉ፤ እንዲሁም የሣር ክዳኖችንና የጭቃ ግድግዳዎችን ጥሰው በመግባት ሰዎችን ይወስዳሉ።”

የጥንቷ ግብፅ ጎተራዎች በቁፋሮ ተገኙ

በደቡባዊ ግብፅ የሚሠሩ የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የአርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች በዚያች አገር እስከዛሬ ከተገኙት ጎተራዎች ሁሉ የሚበልጡ ሰባት የእህል ጎተራዎችን በቁፋሮ አገኙ። በአቅራቢያው የተገኙ ዕደ ጥበባዊ ቅርሶች፣ ጎተራዎቹ የተሠሩት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ1630 እስከ 1520 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደነበረ ለመገመት አስችለዋል። ተመራማሪዎቹ የገመቱት ዘመን ትክክል ከሆነ ጎተራዎቹ በሙሴ ዘመን ነበሩ ማለት ነው። እነዚህ ክብ ጎተራዎች ዲያሜትራቸው ከ5.5 እስከ 6.5 ሜትር፣ ቁመታቸው ደግሞ ቢያንስ 7.5 ሜትር የሚደርስ ሲሆን በወቅቱ የነበረው መንግሥት እህል ለማከፋፈል የገነባው ማዕከል ክፍል ነበሩ። ግኝቱን አስመልክቶ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው ሪፖርት እንደሚናገረው እንዲህ ያሉት ማዕከላት “ከናይል ሸለቆ የሚገኘውን ምርት ለመንግሥት ጥቅም ለማዋል የሚያገለግሉ የማከማቻ ቦታዎች ሆነው ነበር። እህል እንደ ገንዘብ ሆኖ ያገለግል ስለነበር ለፈርዖኖች የሥልጣናቸው የደም ሥር ነበር።” አክሎም ሪፖርቱ “እህል እንደ ገንዘብ ይቆጠር ስለነበረ ጎተራዎቹ እንደ ባንክና የቀለብ ምንጭ ሆነው ያገለግሉ ነበር” ብሏል።

እንደ ብረት የጠነከረ ወረቀት

በስዊድን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ተቋም ውስጥ የሚሠሩ ተመራማሪዎች፣ በእንጨት ሴሉሎስ ውስጥ ያሉት ጭረቶች ተፈጥሯዊ ጥንካሬያቸው እንደተጠበቀ እንዲቆይ በሚያደርግ መንገድ ወረቀት የሚሠራበትን ዘዴ ፈልስፈዋል። ወረቀት ለመሥራት እንጨቱን መፍጨት ይጠይቃል፤ በአሁኑ ጊዜ ይህ የሚከናወንበት ዘዴ የሴሉሎስ ጭረቶችን ስለሚያበላሻቸው ጥንካሬያቸው በእጅጉ ይቀንሳል። የስዊድኑ የተመራማሪዎች ቡድን ግን ለወረቀት መሥሪያ የሚውለውን እንጨት በተለያዩ ኢንዛይሞች ካፈረሰ በኋላ በውኃ ውስጥ በመጨመር እንደ ዕንቁላል መምቻ ያለ ማሽን ተጠቅሞ የሴሉሎስ ጭረቶቹን በቀስታ መለየት ችሏል። ያልተበላሹት ጭረቶች ከውኃው ውስጥ ተንጠፍጥፈው ሲወጡ እርስ በርሳቸው በመጠላለፍ ቀልጦ ከተሠራ የብረት ዕቃ የሚጠነክርና ለግንባታ አገልግሎት ከሚውል ዐረብ ብረት ጋር የሚመጣጠን ጥንካሬ ያለው ወረቀት ይሆናሉ።