በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወላጆች ምን እርዳታ ማበርከት ይችላሉ?

ወላጆች ምን እርዳታ ማበርከት ይችላሉ?

ወላጆች ምን እርዳታ ማበርከት ይችላሉ?

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኝ አንድ የትምህርት ተቋም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን “የመጨረሻ አቅማችሁን ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆናችሁን አሳዩ” በማለት ያበረታታል። አንዳንድ ወጣቶች ግቦቻቸው ላይ ለመድረስ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ከአቅማቸው በላይ ጥረት ያደርጋሉ። ከዚህ በፊት ባለው ርዕስ ላይ የተጠቀሱት ማደለን ለቫይን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “አንዳንድ ትምህርቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚደረግ ጥድፊያ፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚሳተፉባቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ኮሌጅ ለመግባት የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም የግል አስጠኚዎችን በመቅጠር በተቻለ መጠን ከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ ለመርዳት የሚደረገው ጥረት አንድ ላይ ተዳምረው በልጆች ላይ ጫና ያሳድሩባቸዋል። ይህም ብዙ ልጆች ውጥረት ውስጥ እንዲገቡና ጤንነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል።” በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ለአካላዊና ለስሜታዊ ጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ።

ልጅህ በትምህርት ቤት የሚያጋጥመው ውጥረት የሚያሳስብህ ከሆነ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ከአስተማሪዎቹ፣ ከአማካሪዎቹና ከአስተዳደር ሠራተኞች ጋር ተነጋገር። በልጅህ ላይ ያስተዋልከውን ነገር ንገራቸው። ይህ መብትህ መሆኑን አትዘንጋ።

መጽሐፍ ቅዱስ ወላጆች የልጆቻቸውን እድገት በቅርብ እንዲከታተሉ ያበረታታል። ሙሴ ለእስራኤላውያን ወላጆች እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “[የአምላክን ሕጎች] ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።”—ዘዳግም 6:7

ስለ ልጅህ የትምህርት ሁኔታ ትኩረት ሰጥተህ መከታተልህ በሕይወቱ ውስጥ ጣልቃ እንደገባህ ተደርጎ ሊታይ አይችልም። ከዚህ ይልቅ ለልጅህ ፍቅራዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ ያሳያል። እንዲህ ማድረግህ ደግሞ ልጅህ በትምህርት ቤት የሚያጋጥመውን ውጥረት በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

[በገጽ 8 እና 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ልጅህ ምን ያህል ውጥረት እንደሚሰማው ከአስተማሪዎቹና ከአማካሪዎቹ ጋር ተነጋገር