በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ዘኍልቍ 22:21-27ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን የጎደሉትን ነገሮች ቦታ ቦታቸው ላይ ሳልና ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት፦

በለዓም የተናደደው ለምንድን ነው? በለዓም በአህያዪቱ ላይ ስላደረገው ነገር ስታስብ ምን ይሰማሃል? እንደዚህ የተሰማህስ ለምንድን ነው?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 7-8 ሰዎችን መፍራት ምን ሊሆንብህ ይችላል? ምሳሌ 29:․․․

ገጽ 7 ሞኝ ሰው የሚሄደው በምን ውስጥ ነው? መክብብ 2:․․․

ገጽ 7 የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ምን ያመራል? ምሳሌ 21:․․․

ገጽ 22 ሙታን የሚያውቁት ነገር አለ? መክብብ 9:․․․

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ስለ ነቢያት ምን የምታውቀው ነገር አለ?

ኤርምያስ 38:1-13 እንዲሁም 39:15-18ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።

4. ․․․․․

ኤርምያስን ከሞት ያዳነው ማነው? አደጋ ሊያስከትልበት የሚችል ቢሆንም ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?

5. ․․․․․

ከጊዜ በኋላ ኤርምያስ ለዚህ ሰው ምን ነገረው?

ለውይይት፦

ሕይወቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ቢሆንም እንኳ ኤርምያስ የይሖዋን መልእክት ያወጀው ለምንድን ነው? እንደ ኤርምያስ ይሖዋን የምታገለግል ከሆነ ይሖዋ ምን እንደሚያደርግልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ?

▪ መልሶቹ ገጽ 27 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. አህያዪቱ።

2. የበለዓም በትር።

3. የይሖዋ መልአክ።

4. አቤሜሌክ። ኤርምያስ የይሖዋ ነቢይ መሆኑንና ሞት የሚገባው ሰው እንዳልሆነ ያውቅ ነበር።

5. ኢየሩሳሌም ስትጠፋ ይሖዋ አቤሜሌክን እንደሚታደገው ነገረው።