በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

በመጀመሪያ የሐዋርያት ሥራ 3:1-10ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት፦

ሐዋርያት ተአምራት እንዲፈጽሙ ያስቻላቸው ምንድን ነው? ይህስ ለወደፊቱ ምን ተስፋ ይሰጠናል? ፍንጭ፦ ራእይ 21:3, 4ን እና 22:2ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 አንድ ልጅ ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ከሕፃንነቱ ጀምሮ ቢማር ውጤቱ ምን ይሆናል? ምሳሌ 22:․․․

ገጽ 5 አምላክ ከአንድ ሰው ምን ፈጠረ? የሐዋርያት ሥራ 17:․․․

ገጽ 11 መልካም ቃል መናገር ምን ያስገኛል? ምሳሌ 12:․․․

ገጽ 23 በክርስቲያኖች መካከል ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው? ሉቃስ 9:․․․

ስለ መስፍኑ ናዖድ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

መሳፍንት 3:12-30ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።

4. ․․․․․

ከየትኛው ነገድ ነበር?

5. ․․․․․

እስራኤልን ያዳነው ከየትኛው ገዥ ነበር?

6. ․․․․․

እውነት ወይስ ሐሰት? የኖረው ከንጉሥ ዳዊት በፊት ነበር።

ለውይይት፦

መሳፍንት 3:15, 28ን አንብብ። ይሖዋ ናዖድን ያስነሳው ለምን ነበር? ናዖድ ላገኛቸው ድሎች ያመሰገነው ማንን ነበር? አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥምህ ምን ማድረግ አለብህ? ለምን?

▪ መልሱ በገጽ 29 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ጴጥሮስና ዮሐንስ ነበሩ።

2. ሰውየው ሽባ እንጂ ዓይነ ስውር አልነበረም።

3. ሽባው ሰው በቤተ መቅደሱ በር አቅራቢያ እንጂ ከከተማው ውጪ አልነበረም።

4. ብንያማዊ።—መሳፍንት 3:15

5. ዔግሎን።—መሳፍንት 3:14

6. እውነት።