በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ይሖዋ ብቻ ሊከፍተው የሚችል መሳቢያ’

‘ይሖዋ ብቻ ሊከፍተው የሚችል መሳቢያ’

‘ይሖዋ ብቻ ሊከፍተው የሚችል መሳቢያ’

የስድስት ዓመቷ ኤሪካና የአራት ዓመቱ ማቲያ በ2007 አባታቸውን በሞት አጡ። ልጆቹ መጽናናት የቻሉት በትንሣኤ ተስፋ አማካኝነት ነው።—የሐዋርያት ሥራ 24:15

ኤሪካ በተለይ በሲሲሊ በሚገኘው ትምህርት ቤቷ ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለተመሠረተው እምነቷ ለሌሎች መናገር ያስደስታታል። ለምሳሌ፣ አብራት የምትማር ቢአትሪቼ የምትባል አንዲት ልጅ የኤሪካ አባት በሰማይ እንደሆነ ስትነግራት ኤሪካ አባቷ ወደ ሰማይ እንዳልሄደ በደግነት መለሰችላት። በዚህ ጊዜ ቢአትሪቼ “ታዲያ የት ነው ያለው?” በማለት ጠየቀቻት።

ኤሪካ “በመቃብር ውስጥ” በማለት መለሰችላት። በዚህ ጊዜ ቢአትሪቼ መቃብር ምን እንደሆነ ለማወቅ ፈለገች።

ኤሪካም እንዲህ በማለት አብራራችላት፦ “መቃብር እንደሚከፈትና እንደሚዘጋ መሳቢያ ነው። ይህ መሳቢያ አንዴ ከተዘጋ ግን መክፈት አትችይም። አዲሱ ዓለም ሲመጣ ሊከፍተው የሚችለው ይሖዋ ብቻ ነው።”

በመቀጠልም ኤሪካ አብራት ለምትማረው ልጅ የአምላክ ስም ይሖዋ እንደሆነና ምድርን ወደ ገነትነት እንደሚለውጥ እዚያም ሕመም እንደማይኖር እንዲሁም የሞቱት ተመልሰው ሕይወት እንደሚያገኙ ነገረቻት። እነዚህን ነገሮች የሚያብራራ መጽሐፍ በስጦታ መልክ ብትሰጣት እናቷ ትፈቅድላት እንደሆነ ቢአትሪቼን ጠየቀቻት።

ኤሪካ፣ እናቷ እንደፈቀደችላት ስታውቅ ለቢአትሪቼ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ሰጠቻት። ኤሪካ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተማረቻቸውን ነገሮች ለሌሎች መንገሯን የቀጠለች ሲሆን ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ለአስተማሪዋ ሰጥታለች።

እርግጥ ነው፣ ኤሪካና ታናሽ ወንድሟ በአባታቸው ሞት ምክንያት የሚያዝኑበት ጊዜ ቢኖርም የትንሣኤ ተስፋ አጽናንቷቸዋል። እነዚህ ልጆች በዓለም ዙሪያ እንዳሉ ሌሎች ሰዎች የእውነተኛ መጽናኛ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ያመሰግናሉ።—ማቴዎስ 21:16፤ 2 ቆሮንቶስ 1:3, 4

እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ይህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

በየትኛው ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይጥቀሱ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።