በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ ነው ወይስ በፍጥረት?

ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ ነው ወይስ በፍጥረት?

ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ ነው ወይስ በፍጥረት?

በሜክሲኮ የምትኖረው አስፐን፣ የ12 ዓመት ልጅ ሳለች የባዮሎጂ አስተማሪዋ በዝግመተ ለውጥ ሳይሆን በፍጥረት የምታምነው ለምን እንደሆነ ለሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች እንድታስረዳ ጠየቀቻት። አስፐን ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ግሩም ንድፍ ያለው መሆኑ ፈጣሪ መኖሩን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንደሆነ ጥሩ አድርጋ አብራራችላቸው። አስተማሪዋ፣ የአስፐን ወላጆች ጂኦሎጂስቶች መሆናቸውን ስለምታውቅ በቅሪተ አካላት ላይ የሚደረገው ምርምር ሕይወት በፍጥረት እንደተገኘ የሚያረጋግጥ መሆን አለመሆኑን ለማስረዳት በጉዳዩ ላይ ተዘጋጅታ እንድትመጣ ጠየቀቻት።

በቀጣዩ ቀን አስፐን ለናሙና አንዳንድ ቅሪተ አካላትን ወደ ትምህርት ቤት ይዛ በመሄድ በዚህ ረገድ የሚደረገው ምርምር ለዝግመተ ለውጥ ማስረጃ እንደማይሆን ለክፍሉ ተማሪዎች አስረዳች። ከዚህም በተጨማሪ ምርምር የሚደረግበት እያንዳንዱ የቅሪተ አካል ስብስብ በተለያየ ዘመን የኖረ መሆኑ ስለ ፍጥረት ቀናት የሚናገረውን የዘፍጥረት ዘገባ እንደሚደግፍ አብራራችላቸው።

አስፐን ንግግሯን ስታቀርብ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ተገኝተው ስለነበር በፍጥረት ላይ ያላትን እምነትና ያብራራችበትን መንገድ በማድነቅ አመሰገኗት። የባዮሎጂ አስተማሪዋም ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው የሚለው እምነት ሁሉንም ነገር ግልጽ እንደሚያደርገው በሌላ በኩል ግን ዝግመተ ለውጥ ብዙ ጥርጣሬዎችን እንደሚፈጥር ተናገረች። ከዚያም አስፐን ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር፣ ለአስተማሪዋና ለክፍል ተማሪዎቿ ሳይንስ ፍጥረትን እንደሚደግፍ የሚያስረዳ ጽሑፍ ሰጠቻቸው።

እርስዎስ፣ ‘ፈጣሪ መኖሩን የሚያረጋግጡ ተጨባጭነት ያላቸው ሳይንሳዊ ማስረጃዎች ይኖሩ ይሆን? ፈጣሪ ካለ ደግሞ ስለ እኛ ያስባል ብለን እንድናምን የሚያደርገን ምክንያት ይኖር ይሆን?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማወቅ እዚህ ላይ የሚታየውን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲያነቡ እንጋብዝዎታለን።

ይህ መጽሐፍ እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

በየትኛው ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይግለጹ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።