በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

የወጣቶች ጥያቄ . . . ወንድሜ ወይም እህቴ ሕይወታቸውን ቢያጠፉስ? (ሰኔ 2008) ታላቅ እህቴ ከመሞቷ በፊት ለአምስት ዓመታት ያህል ከመንፈስ ጭንቀት ጋር ትታገል ነበር። ሕመሙ ምን ይህል እንሚያሠቃያት ስለተመለከትኩ ‘ሕይወቷ ምንኛ መራራ ነበር!’ ብዬ አስብ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ንቁ! መጽሔት ከሟቹ ጋር ያሳለፍናቸውን አስደሳች ትዝታዎች እንድናስታውስ ያበረታታል። ከእህቴ ጋር ያሳለፍኳቸውን አስደሳች ትዝታዎች ማስታወስ ስጀምር ‘ሕይወቷ መራራ’ እንዳልነበረ ተገነዘብኩ። አስቸጋሪ ከሆኑት ጊዜያት ይልቅ ደስተኛ የነበረችባቸው ጊዜያቶች ስለሚበልጡ እህቴ ያሳለፈችው ሕይወት አስደሳች ነበር ማለት እችላለሁ።

ኤስ. ዋይ.፣ ጃፓን

የወጣቶች ጥያቄ . . . ወላጆቼ እምነት የማይጥሉብኝ ለምንድን ነው? (ሚያዝያ 2008) በንቁ! መጽሔት ላይ የሚወጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ማንበቤና ተግባራዊ ማድረጌ፣ የወላጆቼን አመኔታ እንዳተርፍ የረዳኝ ከመሆኑም ባሻገር ወደ ጉልምስና መድረስ ዘው ተብሎ እንደሚገባበት በር ሳይሆን ቀስ በቀስ እንደሚወጣ ደረጃ መሆኑን እንድገነዘብ አስችሎኛል። ተጨማሪ ነፃነት ማግኘት የምፈልግ ከሆነ የወላጆቼን አመኔታ ማትረፍ እንዳለብኝ ተገንዝቤያለሁ። ቤት ውስጥ ያሉብኝን የዕለት ተዕለት ሥራዎች አልፎ ተርፎም በትምህርት ቤት የሚሰጡኝን የቤት ሥራዎች ጥንቅቅ አድርጌ መሥራት ይኖርብኛል። እንዲህ የመሰሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ስለምታወጡልን ከልብ በመነጨ ስሜት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ቲ. ኤል.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

አልቢኒዝም የሚያስከትለውን ችግር ተቋቁሞ መኖር (ሐምሌ 2008) እንደ ጆን ሁሉ እኔም አልቢኒዝም የተባለው የጤና እክል አለብኝ፤ በመሆኑም ይህን ርዕሰ ጉዳይ በማውጣታችሁ በጣም አመሰግናችኋለሁ። ስለ አልቢኒዝም የሚናገር ትክክለኛና እውነተኛ እንዲሁም በቁም ነገር የታሰበበት ብሎም ትምህርት ሰጪና ጠቃሚ የሆነ መረጃ የያዘ ርዕሰ ጉዳይ ማውጣታችሁ በጣም የሚደነቅ ነው። ጓደኞቼ ይህን ርዕሰ ትምህርት ማንበባቸው ስላለሁበት ሁኔታ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ቲ. ኤም.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ከአውሎ ነፋስ ይበልጥ ኃይል ያለው ፍቅር! (ነሐሴ 2008) እንዲህ ያሉ ርዕሶች ወደፊት ምን ያጋጥመኝ ይሆን ብዬ ከመስጋት ይልቅ በአምላክ ላይ ሙሉ በሙሉ መታመን እንዳለብኝ ያስታውሱኛል። አማኝ ያልሆኑት የወላጆቼ ቤት ከሦስት ዓመት በፊት በጎርፍ ከተወሰደ በኋላ እንዲህ ያለውን የወንድማማች ፍቅር መመልከት ችያለሁ። በአካባቢው የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች በፍጥነት መጥተው ረድተውናል። ይሖዋ በእሱ ድርጅት ውስጥ እንድታቀፍ ስለፈቀደልኝ አመሰግነዋለሁ።

ዲ. ደብሊው.፣ ፖላንድ

የበቆሎ አስደናቂነት (ነሐሴ 2008) ቤተሰቦቼ በጓሮ የአትክልት ቦታችን ላይ ጥቂት የበቆሎ ዘር ቢዘሩም እኩል መጠን ያላቸው ፍሬዎች ያሉት በቆሎ ማግኘት አልቻሉም ነበር። አሁን ግን ይህን ርዕሰ ጉዳይ በማንበባችን የችግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ መረዳት ችለናል። የምንዘራው አምስት ወይም ስድስት ፍሬ ብቻ በመሆኑ በቆሎዎቹ በትልቅ ማሳ ላይ እንደሚዘሩት በቆሎዎች በሚገባ መራባት አልቻሉም። ባለፈው ዓመት በእያንዳንዱ ዘለላ ላይ ያለውን “የበቆሎ ፀጉር” ተጠቅመን በቆሎዎቹን በጥንቃቄ በማራባታችን እኩል መጠን ያላቸው ፍሬዎች ያሉት ጣፋጭ በቆሎ ማግኘት ችለናል። በጣም እናመሰግናችኋለን።

አር. ደብሊው.፣ ጃፓን