በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የባሕር ላይ ዓምድ

የባሕር ላይ ዓምድ

የባሕር ላይ ዓምድ

ውኃ በነፋስ ኃይል እየሾረ ወደ ላይ ሲቆም አይተህ ታውቃለህ? ታኅሣሥ 25, 2005 በታሂቲ የባሕር ዳርቻ አካባቢ እንዲህ ያለ ሁኔታ ተከስቶ ነበር። ውኃው በነፋስ ኃይል ከባሕር ተነስቶ እንደ አዙሪት እየሾረ ወደ ሰማይ የነጎደ ሲሆን ይህ ትዕይንት ለ30 ደቂቃ ያህል ቆይቶ ነበር። ከዚያም ቀስ በቀስ መልኩ ወደ ነጭነት ተቀይሮ ጠፋ።

እንዲህ ያለው ትዕይንት አንዳንድ ጊዜ የውኃ ላይ አውሎ ነፋስ (ቶርኔዶ) ተብሎ ይጠራል፤ ይሁን እንጂ ይህ ነፋስ የቶርኔዶን ያህል ኃይለኛ አይደለም። ብዙውን ጊዜ የሚቆየው ለአሥር ደቂቃ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት ያህል ሊቆይ ይችላል። ይህ ሁኔታ የሚፈጠረው በባሕር ላይ ስለሆነ ሊታይ የሚችለው በአጋጣሚ ነው። ይህ ደግሞ በአየር ትንበያ ሙያ ለተሰማሩ ሰዎች ስለዚህ የባሕር ላይ ነፋስ የበለጠ እንዳያውቁ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ነፋሱ በጣም በፍጥነት ከሚበር ባቡር ጋር የሚመሳሰል ኃይለኛ ድምፅ ሊኖረው ይችላል።

በጥንት ዘመን የኖረና የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነ አንድ መዝሙራዊ የደረሰበትን የስሜት መታወክ ሲገልጽ “በፏፏቴህ ማስገምገም፣ አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል” ብሏል። (መዝሙር 42:7) እዚህ ላይ “ፏፏቴ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ከላይ የተገለጸውን ዓይነት እንደ ዓምድ የሚቆም አውሎ ነፋስ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፤ ያም ሆነ ይህ መዝሙራዊው እንዲህ ያለውን ክስተት በወቅቱ የተሰማውን ስሜት ለመግለጽ ተጠቅሞበታል። መዝሙራዊው ነፍሱ ‘እንደምተክዝ’ እና በውስጡ ‘እንደምትታወክ’ ተናግሯል። ሆኖም ከአምላኩ መጽናኛ አግኝቷል። ነፍሱን “ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣ አዳኜና አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁ” ብሏታል።—መዝሙር 42:11

እንደ መዝሙራዊው ሁሉ እኛም በባሕር ላይ ከሚፈጠረው አውሎ ነፋስ ጋር ሊመሳሰል የሚችል አስጨናቂ ሁኔታ ሊያጋጥመን ይችላል። ይሁን እንጂ አምላክን በተስፋ የምንጠባበቅ ከሆነ ታላቅ መዳን እናገኛለን።