በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

5ኛው ቁልፍ፦ ምክንያታዊነት

5ኛው ቁልፍ፦ ምክንያታዊነት

5ኛው ቁልፍ፦ ምክንያታዊነት

“ምክንያታዊነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን።” —ፊልጵስዩስ 4:5

ምን ማለት ነው? የተሳካ ትዳር ባላቸው ቤተሰቦች ውስጥ ባልና ሚስት ስህተት ሲሠሩ አንዳቸው ለሌላው ይቅርታ ያደርጋሉ። (ሮም 3:23) በተጨማሪም በልጆቻቸው ላይ ከልክ በላይ ጥብቅ አይሆኑም፤ ወይም መረን አይለቋቸውም። እንዲሁም በቤት ውስጥ መጠነኛ ሕጎች ያወጣሉ። አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም “በመጠኑ” እርማት ይሰጣሉ።—ኤርምያስ 30:11

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ “ከላይ የሆነው ጥበብ . . . ምክንያታዊ [ነው]” ይላል። (ያዕቆብ 3:17) አምላክም ቢሆን ፍጹም ካልሆኑ ሰዎች ፍጽምና አይጠብቅም። ታዲያ ባልና ሚስት አንዳቸው ከሌላው ፍጽምና መጠበቃቸው ምክንያታዊ ነው? በእርግጥም ጥቃቅን ስህተቶችን መለቃቀም ቅሬታን ከመፍጠር በቀር የሚፈይደው ነገር አይኖርም። ‘ሁላችንም ብዙ ጊዜ እንደምንሰናከል’ አምነን መቀበላችን የተሻለ ነው።—ያዕቆብ 3:2

የተሳካ ትዳር ያላቸው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያታዊነት ያንጸባርቃሉ። የሚሰጡት ተግሣጽም ከልክ ያለፈ አይደለም፤ ወይም ደግሞ ‘በቀላሉ የማይደሰቱ’ ዓይነት ሰዎች አይደሉም። (1 ጴጥሮስ 2:18) ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ላስመሠከሩ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ልጆቻቸው ነፃነት ይሰጣሉ እንጂ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን ለመቆጣጠር አይሞክሩም። ወላጆች በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኝ ልጃቸውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር መሞከራቸው ከድካም በቀር የሚፈይድላቸው ነገር እንደማይኖር አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ ገልጿል።

ይህን ለማድረግ ሞክር፦ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ምን ያህል ምክንያታዊ እንደሆንክ ገምግም።

የትዳር ጓደኛህን ለመጨረሻ ጊዜ ያመሰገንካት መቼ ነው?

የትዳር ጓደኛህን ለመጨረሻ ጊዜ የተቸሃትስ መቼ ነበር?

ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። ለመጀመሪያው ጥያቄ መልስ መስጠት ካዳገተህና ለሁለተኛው ጥያቄ ግን ያላንዳች ችግር መልስ ከሰጠህ ከትዳር ጓደኛህ በምትጠብቀው ነገር ይበልጥ ምክንያታዊ ለመሆን ግብ አውጣ።

ሁለታችሁም በዚህ ረገድ ምን ማድረግ እንደምትችሉ ከትዳር ጓደኛህ ጋር ለምን አትወያይም?

በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችሁ ኃላፊነት የሚሰማቸው ወጣቶች መሆናቸውን ካሳዩ በምን ረገድ ነፃነት ልትሰጧቸው እንደምትችሉ አስቡ።

ቤት እንዲገቡ የሚጠበቅባቸውን ሰዓት በተመለከተ ወይም በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ከሚገኙ ልጆቻችሁ ጋር ግልጽ ውይይት ለምን አታደርጉም?

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጠንቃቃ የሆነ አሽከርካሪ እንደሚያደርገው ምክንያታዊ የሆነ የቤተሰብ አባልም ለሌሎች ፍላጎት ቅድሚያ ይሰጣል