በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

7ኛው ቁልፍ፦ ጽኑ መሠረት

7ኛው ቁልፍ፦ ጽኑ መሠረት

7ኛው ቁልፍ፦ ጽኑ መሠረት

ምን ማለት ነው? አንድ ቤት ለብዙ አሥርተ ዓመታት ጸንቶ የሚቆመው እንዲሁ እንዳልሆነ ሁሉ ጠንካራ ቤተሰቦችም ጸንተው የሚቀጥሉት እንዲያው በአጋጣሚ አይደለም። አንድ ጠንካራ ሕንፃ ጽኑ መሠረት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ጠንካራ ቤተሰብም ጽኑ መሠረት ያስፈልገዋል። የተሳካ የቤተሰብ ሕይወት፣ ጠቀሜታው በተረጋገጠ መመሪያ ላይ የተመሠረተ ነው።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ስለ ቤተሰብ ሕይወት ምክር የሚሰጡ መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በብዛት ይገኛሉ። አንዳንድ የትዳር አማካሪዎች ችግር የገጠማቸውን ባልና ሚስት አብረው እንዲኖሩ ሲያበረታቱ ሌሎች ደግሞ እንዲፋቱ ይመክሯቸዋል። ባለሙያዎቹ ራሳቸውም እንኳ ይህን በተመለከተ ያላቸውን አስተሳሰብ ከጊዜ በኋላ ይለውጣሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል ልዩ ሥልጠና ያገኘች አንዲት ዝነኛ አማካሪ ሥራዋን በጀመረችበት ወቅት ምን አመለካከት እንደነበራት በ1994 እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ልጆች ደስታ በሌለበት ትዳር ውስጥ ከሚያድጉ ይልቅ ደስተኛ ከሆኑ ነጠላ ወላጆች ጋር ቢያድጉ ይሻላቸዋል። ከመጥፎ ትዳር ጋር ከመታገል መፋታት ይሻላል ብዬ አስብ ነበር።” ከሃያ ዓመት የሥራ ልምድ በኋላ ግን አመለካከቷ ተለወጠ። “ፍቺ የብዙ ልጆችን ሕይወት ያበላሻል” ብላለች።

የሰዎች አመለካከት በየጊዜው ይለዋወጣል፤ ይሁንና በጣም ጥሩ የሚባለው ምክር ሁልጊዜ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት መሠረታዊ መመሪያዎች ጋር በሆነ መልኩ ይመሳሰላል። እነዚህን ተከታታይ ርዕሶች ስታነብ ከገጽ 3 እስከ 8 አናት ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት እንደሰፈረ አስተውለህ ይሆናል። እንዲህ ዓይነቶቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ብዙዎች የተሳካ የቤተሰብ ሕይወት እንዲኖራቸው ረድተዋቸዋል። የተሳካላቸው ቤተሰቦችም ቢሆኑ እንደ ሌሎች ቤተሰቦች ችግር ያጋጥማቸዋል። ልዩነቱ ለትዳርና ለቤተሰብ ሕይወት ጽኑ መሠረት የሚሆኑ መመሪያዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘታቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን መመሪያ የሚሰጥ መሆኑ የሚጠበቅ ነገር ነው፤ ምክንያቱም የቤተሰብ መሥራች የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት የሆነው ይሖዋ አምላክ ነው።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17

ይህን ለማድረግ ሞክር፦ ከገጽ 3 እስከ 8 አናት ላይ ደመቅ ብለው የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በወረቀት ላይ ጻፍ። አንተን የረዳህ ሌላ ጥቅስ ካስታወስክ እሱንም በዝርዝሩ ውስጥ ጨምረው። ከዚያም ወረቀቱን በቅርብ ልታገኘው በምትችልበት ቦታ አስቀምጠውና ዘወትር ተመልከተው።

ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። በራስህ ቤተሰብ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ።

[በገጽ 8 እና 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጽኑ መሠረት ያለው ቤት አደገኛ የአየር ጠባይ መቋቋም እንደሚችል ሁሉ ቤተሰብህም በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጽኑ ሆኖ ከተገነባ ከባድ ችግሮችን መቋቋም ይችላል