በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ ወዳጅ መሆን ትፈልጋለህ?

የአምላክ ወዳጅ መሆን ትፈልጋለህ?

የአምላክ ወዳጅ መሆን ትፈልጋለህ?

ከላይ ለቀረበው ጥያቄ ምን መልስ ትሰጣለህ? የሜክሲኮ ግዛት በሆነችው በጉዌሬሮ ራቅ ብሎ በሚገኝ አካባቢ የምትኖር አንዲት ወጣት የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል ብላ እንደማታስብ ተናግራ ነበር። ይህን የተናገረችው፣ የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑ ሁለት ሴቶች የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! የተሰኘውን በአፍ መፍቻ ቋንቋዋ የተዘጋጀ ብሮሹር ባሳዩዋት ጊዜ ነበር። ይህች ወጣት መንግሥት ያሳተማቸው ካልሆነ በቀር የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ በሆነው በታልፓኔክ የተዘጋጁ ጽሑፎችን ከዚህ በፊት አይታ ስለማታውቅ ይህ ብሮሹር በቋንቋዋ መኖሩ በጣም አስገረማት።

ሁለቱ ሴቶች ይህ ብሮሹር አምላክን ለማወቅ የሚያስችላት በመሆኑ የዚህ ጽሑፍ መዘጋጀት በራሱ ፈጣሪ እሷንም እንደሚወዳት የሚያሳይ ማስረጃ እንደሆነ ለወጣቷ ነገሯት። እሷም “አምላክ ወዳጁ እንድትሆን ይጋብዝሃል” የሚለውን የመጀመሪያውን ርዕሰ ትምህርት በጉጉት ማንበብ ጀመረች። አንብባው ስትጨርስ “እኔም የአምላክ ወዳጅ መሆን እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ ልታመጡልኝ ትችላላችሁ?” ብላ ጠየቀቻቸው። የይሖዋ ምሥክሮቹ ተመልሰው ሲሄዱ ለወጣቷ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘውላት መጡ፤ በዚህ ጊዜ እናትየው ትንሽ ቆይተው ተጨማሪ ነገር እንዲያስተምሯቸው ጠየቀቻቸው።

ታልፓኔክ፣ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! የሚለው ብሮሹር ከተዘጋጀባቸው በሜክሲኮ የሚኖሩ የአሜሪካ ሕንዶች ከሚናገሯቸው 17 ቋንቋዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። ይህ ብሮሹር በመላው ዓለም (ብሬይልን ጨምሮ) በ278 ቋንቋዎች ይገኛል። እርስዎም ይህን ብሮሹር ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።