በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንቁ! በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ከሞት አዳነ

ንቁ! በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ከሞት አዳነ

ንቁ! በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ ከሞት አዳነ

በሜክሲኮ የምትኖር አኒታ የተባለች የሦስት ልጆች እናት አራተኛ ልጅ እንዳረገዘች አወቀች። * አኒታ ሌላ ልጅ መውለድ እንደማትፈልግና ጽንሱን ለማስወረድ ማንኛውንም ነገር እንደምታደርግ ሌላው ቀርቶ ሕይወቷን እንኳ ከማጥፋት እንደማትመለስ ለባሏ ነገረችው። በወቅቱ አኒታ ከአንዲት የይሖዋ ምሥክር ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ታጠና የነበረ ቢሆንም እምብዛም ለውጥ አታደርግም ነበር። “ግትር ነበርኩ” በማለት ተናግራለች።

አኒታን መጽሐፍ ቅዱስ የምታስጠናት የይሖዋ ምሥክር ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አብራራችላት። ለምሳሌ ያህል፣ የፅንሱ ሕይወት በአምላክ ዓይን ቅዱስ እንደሆነ ገለጸችላት። በጥንቷ እስራኤል አንድ ሰው አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ላይ ጉዳት ቢያደርስባትና እሷ ወይም ገና ያልተወለደው ልጇ ቢሞቱ ጉዳት ያደረሰባት ሰው እንደ ነፍሰ ገዳይ ሊፈረድበት እንደሚገባ የአምላክ ሕግ ደንግጓል። (ዘፀአት 21:22, 23) * አኒታ ግን ይህን ሁሉ ለመስማት ፈቃደኛ አልነበረችም። ፅንሱን ለማስወረድ ቆርጣ ነበር።

አኒታ እንዲህ በማለት ትናገራለች፦ “አንድ ሰው፣ ፅንሱን ወዲያውኑ የሚያስወርድ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት እንዳለ ነገረኝ። ስለዚህ መድኃኒቱን ገዛሁና አንድ ወዳጄ መርፌውን እንዲወጋኝ ጠየቅሁት። መርፌውን ቢወጋኝም ፅንሱ አልወረደም። በኋላ እንደተረዳሁት ግን ወዳጄ በዚህ ድርጊት ተባባሪ መሆን ስላልፈለገ የወጋኝ መድኃኒቱን ሳይሆን ውኃ ነበር።”

ያም ሆኖ አኒታ በሐሳቧ ገፋችበት። በአራተኛ ወሯ ውርጃ ሊፈጽምላት ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሐኪም አገኘች። ቀጠሮው ከመድረሱ ስድስት ቀን ቀደም ብሎ አኒታን የምታስጠናት የይሖዋ ምሥክር በግንቦት 22, 1980 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ላይ የወጣውን “የአንድ ፅንስ የዕለት ማስታወሻ” የሚለውን ርዕስ እንድታነብ ለአኒታ ሰጠቻት። “የዕለት ማስታወሻው” የሚደመደመው “ዛሬ እናቴ ገደለችኝ” በሚሉት ቃላት ነበር። እነዚህ ቃላት አኒታን በጣም ስላስደነገጧት ለረጅም ሰዓታት አለቀሰች። “ይህ ርዕስ በመጨረሻ ዓይኔን ከፈተልኝ” ብላለች።

አኒታ ጤናማ የሆነች ልጅ ወለደች። አኒታ “በአሁኑ ጊዜ ይሖዋን የማወቅ መብት ያገኘሁ ሲሆን እሱንም ከልቤ እወደዋለሁ” ብላለች። አኒታ፣ ልጇም ይሖዋን እንድትወደው የአምላክን ቃል እያስተማረቻት ነው። ልጅቷም በሕይወት ለመኖሯ በእርግጥም ሊመሰገን የሚገባው ይሖዋ እንደሆነ በግልጽ ትናገራለች። ይህን ያለችው በመጀመሪያ ደረጃ የሕይወት ምንጭ እሱ ስለሆነ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በንቁ! መጽሔት ላይ የወጣው በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው ትምህርት ከሞት ስላዳናት ነው።

[የግርጌ ማስታወሻዎች

^ አን.2 ስሟ ተለውጧል።

^ አን.3 እዚህ ጥቅስ ላይ የተሠራበት የዕብራይስጥ ቃል የእናቲቱን ወይም የልጁን ሞት ያመለክታል።