በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሻርክ ቆዳ

የሻርክ ቆዳ

ንድፍ አውጪ አለው?

የሻርክ ቆዳ

የሻርክ ቆዳ መጀመሪያ ሲታይ ለስላሳ ይመስላል። ከጅራቱ ወደ ጭንቅላቱ አቅጣጫ በእጅህ ብትዳስሰው ግን (ጉዳት እንዳይደርስብህ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው) የሻርክ ቆዳ እንደ ብርጭቆ ወረቀት የሚሻክር እንደሆነ ትገነዘባለህ። *

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ቆዳው ሻካራ እንዲሆን ያደረጉት ሰርጎድ ያሉ ጥቃቅን ቅርፊቶች ሻርኩን በሁለት መንገድ ይጠቅሙታል። አንደኛ፣ ቅርፊቶቹ እንደ ቦይ በመሃላቸው ውኃ ስለሚያሳልፉ ሻርኩ ብዙ ጉልበት ሳያስፈልገው በቀላሉ መዋኘት እንዲችል ይረዱታል። ሁለተኛ ሻርኩ በሚዋኝበት ጊዜ ቅርፊቶቹ ስለሚንቀሳቀሱ ጥገኛ ተውሳኮች በሻርኩ ቆዳ ላይ ተለጥፈው መኖር አመቺ አይሆንላቸውም።

ሰዎች የሻርክ ቆዳ ያሉትን አንዳንድ ገጽታዎች በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት አድርገዋል። ለምሳሌ ሳይንቲስቶች ከሻርክ ቆዳ ጋር በሚመሳሰል መንገድ የሠሩት የዋና ልብስ የዋናተኛውን ፍጥነት በሦስት በመቶ ገደማ ይጨምራል። ሳይንቲስቶች በዚሁ ዘዴ በመጠቀም ፈጣን የሆኑ መኪኖችንና ጀልባዎችን መሥራት እንደሚቻል ያምናሉ።

በተጨማሪም ተመራማሪዎች ጀልባዎች ላይ ጥገኛ ሕዋሳት እንዳይለጠፉ ለመከላከል ሲባል ጀልባዎቹን መርዛማ ቀለሞች ከመቀባት ይልቅ የሻርክ ቆዳን አፈጣጠር በመኮረጅ ጥገኛ ሕዋሳትን የሚከላከል አካባቢን የማይበክል ሽፋን መሥራት እንደሚቻል ተስፋ ያደርጋሉ። ከዚህም ሌላ የሻርክ ቆዳ የተሠራበትን መንገድ መሠረት በማድረግ በሆስፒታል የሚያጋጥሙ ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስ የሚረዱ የሕክምና መሣሪያዎችን ለመሥራት ያስባሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ኃይል ቆጣቢ የሆነውና ብክለት የማያስከትለው የሻርክ ቆዳ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.3 ከጭንቅላቱ ወደ ጅራቱ አቅጣጫ ሲዳሰስ ግን የቆዳው ሻካራነት አያስታውቅም።

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሻርክ ቅርፊት ጎልቶ ሲታይ

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ቅርፊት፦ © Eye of Science/Photo Researchers, Inc.; ሻርክ፦ © Image Source/age fotostock