ኢየሱስ ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል
ኢየሱስ ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው “ለማገልገልና በብዙዎች ምትክ ነፍሱን ቤዛ አድርጎ ለመስጠት እንጂ እንዲገለገል” እንዳልሆነ ለተከታዮቹ ነግሯቸው ነበር። (ማቴዎስ 20:28) በእርግጥም ለሌሎች ጥቅም ሲል በፈቃደኝነት ሕይወቱን አሳልፎ ሰጥቷል።
ኢየሱስ በመሞት ቤዛ የከፈለው እንዴት ነው? ይህን ማድረጉስ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠው ለእነማን ነው? የእሱ ሞት ለእርስዎ ምን ጥቅም ሊያስገኝ ይችላል?
የይሖዋ ምሥክሮች ከእነሱ ጋር በዚህ መታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝተው መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ እንዲመረምሩ በደስታ ይጋብዝዎታል። በዚህ ዓመት የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የሚውለው ማክሰኞ፣ መጋቢት 30, 2010 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መጋቢት 21, 2002) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። በዚህ ስብሰባ ላይ ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ መልሶች ይሰጣሉ።
እርስዎም በቤትዎ አቅራቢያ በሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች አዳራሽ ውስጥ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ መገኘት ይችላሉ። ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክዎ በአካባቢዎ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ያነጋግሩ።