በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ጥሩ ውሳኔ ነበር?

ማርቆስ 14:66-72ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. በሥዕሉ ላይ ያለው ሁኔታ የተከናወነው የት ነበር?

ፍንጭ፦ ማርቆስ 14:53, 54ን አንብብ።

․․․․․

2. ጴጥሮስ፣ ሰዎች የኢየሱስ ተከታይ እንደሆነ ሲነግሩት ምን አደረገ?

․․․․․

3. ለሁለተኛ ጊዜ ዶሮ ሲጮህ ምን ሆነ?

․․․․․

ለውይይት፦

ጴጥሮስ እንዲህ ዓይነት እርምጃ የወሰደው ለምን ይመስልሃል? አንተስ እንዲህ ያለ ስህተት እንዳትፈጽም ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. ኢዮሣፍጥ በይሁዳ የነበረውን የፍርድ ሁኔታ ያስተካከለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 2 ዜና መዋዕል 19:5-11ን አንብብ።

․․․․․

5. ኢዮሣፍጥ ምን ስህተት ሠራ?

ፍንጭ፦ 2 ዜና መዋዕል 18:1-3ን እና 19:1-3ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ጓደኛን በመምረጥ ረገድ ከኢዮሣፍጥ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 15:33ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 4 ራሳችንን ከምን ነገር ማንጻት ይገባናል? 2 ቆሮንቶስ 7:․․․

ገጽ 5 ሁለት ሰዎች አብረው ምን ማድረግ ይችላሉ? መክብብ 4:․․․

ገጽ 19 ጥበበኞች በምን ላይ ተስፋቸውን አይጥሉም? 1 ጢሞቴዎስ 6:․․․

ገጽ 27 የበለጠ ደስታ የምታገኘው ምን ስታደርግ ነው? የሐዋርያት ሥራ 20:․․․

● መልሱ በገጽ 24 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ።

2. ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደማያውቀው በመናገር ካደ።

3. ጴጥሮስ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

4. ኢዮሣፍጥ አምላክን የሚፈሩ ዳኞች በከተሞች እንዲሁም ሌዋውያንንና ካህናትን በኢየሩሳሌም በመሾም።

5. ክፉ ከነበረው ንጉሥ ከአክዓብ ጋር ወዳጅነት መሠረተ።