በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጠንካራ ፍላጎት አዳብር

ጠንካራ ፍላጎት አዳብር

ጠንካራ ፍላጎት አዳብር

“ማጨስ በማቆም ረገድ ከተሳካላቸው ሰዎች ማየት እንደሚቻለው ሲጋራ ማጨስ ለማቆም የሚያስፈልገው ብቸኛውና ዋነኛው ባሕርይ የልብ ቁርጠኝነት ነው።” —“ስቶፕ ስሞኪንግ ናው!”

ገሩን በአጭሩ ለማስቀመጥ፣ ማጨስ ለማቆም ከፈልግክ ቢያንስ ቢያንስ ጠንካራ ፍላጎት ሊኖርህ ይገባል። ታዲያ ጠንካራ ፍላጎት ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ፣ ማጨስ ብታቆም ምን ያህል የተሻልክ ሰው ልትሆን እንደምትችል አስብ።

ከወጪ ትድናለህ። በቀን አንድ ፓኮ የማጨስ ልማድ ያለው ሰው በዓመት በሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ያወጣል። “ምን ያህል ገንዘብ ለትንባሆ እንደማጠፋ ተገንዝቤ አላውቅም ነበር።”—ግያኑ፣ ኔፓል

በሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለህ። “መኖር የጀመርኩት ማጨስ ካቆምኩ በኋላ ነው ማለት እችላለሁ፤ ሕይወቴ ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻለ መጥቷል።” (ረጂነ፣ ደቡብ አፍሪካ) ሰዎች ማጨስ ሲያቆሙ ጣዕም የመለየትና የማሽተት ችሎታቸው በከፍተኛ ደረጃ ይሻሻላል፤ እንዲሁም የተሻለ አቅም የሚኖራቸው ሲሆን መልካቸውም እየተመለሰ ይመጣል።

ጤንነትህ ሊሻሻል ይችላል። “በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ማጨስ ሲያቆሙ ጤንነታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ፈጣን መሻሻል ያሳያል።”—የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል

በራስ የመተማመን ስሜትህ ከፍ ይላል። “ትንባሆ ጌታዬ እንዲሆን ስላልፈልግኩ ማጨስ አቆምኩ። በገዛ ሰውነቴ ላይ ጌታ መሆን እንዳለብኝ ተሰማኝ።”—ሄኒንግ፣ ዴንማርክ

ቤተሰቦችህና ወዳጆችህ ተጠቃሚ ይሆናሉ። “ማጨስ . . . በአካባቢህ የሚኖሩ ሰዎችን ጤንነትም ይጎዳል። . . . ከሚያጨሱ ሰዎች የሚወጣው የሲጋራ ጭስ በየዓመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ . . . የማያጨሱ ሰዎች በሳንባ ካንሰርና በልብ ሕመም እንዲሞቱ ምክንያት መሆኑን ጥናቶች አረጋግጠዋል።”—የአሜሪካ የካንሰር ማኅበር

ፈጣሪህን ታስደስታለህ። ‘የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ሥጋን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።’ (2 ቆሮንቶስ 7:1) “ሰውነታችሁን . . . ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው . . . አድርጋችሁ [አቅርቡ]።”—ሮም 12:1

“አምላክ ሰውነትን የሚያረክሱ ነገሮችን እንደሚጠላ ስገነዘብ ማጨሴን ወዲያውኑ ለማቆም ወሰንኩ።”—ሲልቭያ፣ ስፔን

ይሁንና ከፍተኛ ፍላጎት ማዳበር በራሱ በአብዛኛው በቂ አይደለም። የቤተሰቦቻችንና የወዳጆቻችንን ጨምሮ የሌሎች ሰዎች እርዳታም ሊያስፈልገን ይችላል። ታዲያ እኛን ለመርዳት ምን ማድረግ ይችላሉ?