‘ጠቃሚ በሆነ ትምህርት እንደተሞላ ውድ ሣጥን ነው’
‘ጠቃሚ በሆነ ትምህርት እንደተሞላ ውድ ሣጥን ነው’
● በኒው ሀምፕሻየር፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ባልና ሚስት እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “ልጆች በማሳደግ ላይ የምንገኝ ሰዎችን የሚረዱ በርካታ ርዕሰ ትምህርቶችን ስለምታወጡ ያለንን ከፍ ያለ አድናቆት መግለጽ እንፈልጋለን። ሶፊያ የምትባል የአራት ዓመት ልጅ አለችን፤ ይህች ልጅ ብዙ ትምህርት በምትቀስምበት በዚህ ዕድሜዋ ጠቃሚ እውነቶችን በአእምሮዋና በልቧ ላይ ለመቅረጽ የሚያስችል የማሠልጠኛ ጽሑፍ እንዳገኘን ይሰማናል።”
ደብዳቤው በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ “ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተሰኘው መጽሐፍ ለእኛም ሆነ ለልጃችን በሚጠቅም ትምህርት እንደተሞላ ውድ ሣጥን ነው ማለት ይቻላል። በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያሉት ሥዕሎች እስከ ዛሬ ካየናቸው ሥዕሎች ሁሉ የሚበልጡ ውብ የገነት መግለጫዎች ናቸው! ትንሿ ልጃችን ሥዕሎቹን ደግማ ደጋግማ አተኩራ ስለምትመለከት የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ በአእምሮዋ ተቀርጿል።”
ከታላቁ አስተማሪ ተማር በተባለው መጽሐፍ ላይ በሚገኘው “አምላክ በሚያመጣው ሰላማዊ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ትችላለህ” በሚለው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ተስፋዎች ውብ በሆኑ ሥዕሎች ተገልጸዋል።
እርስዎም ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለውን ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ይህ ሥዕል በመጽሐፉ ውስጥ በገጽ 254 ላይ ይገኛል