በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምሩት እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምሩት እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምሩት እንዴት ነው?

ብዙውን ጊዜ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በተባለው የማስጠኛ መሣሪያ አማካኝነት ርዕስ በርዕስ ያስተምራሉ። ይህ የማስጠኛ መጽሐፍ ካሉት 19 ምዕራፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

“አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?”

“ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?”

“ሙታን የት ናቸው?”

“የምንኖረው ‘በመጨረሻው ዘመን’ ውስጥ ነው?”

“አምላክ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው?”

“የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?”

ተማሪዎች ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ማበረታቻ የሚሰጣቸው ሲሆን የጥያቄያቸውን መልስ እነሱ ራሳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲመለከቱ ይደረጋል። ከጊዜ በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ባገኙት እውቀት ላይ ተመሥርተው የትኛውን ሃይማኖት መከተል እንዳለባቸው እነሱ ራሳቸው መወሰን ይችላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት አሊያም የማስጠኛውን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።