በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አስተማሪዎች የሚያስተውሉት ልዩነት

አስተማሪዎች የሚያስተውሉት ልዩነት

አስተማሪዎች የሚያስተውሉት ልዩነት

የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ኢሬና የምትኖረው ቡልጋሪያ ውስጥ በምትገኘው ኩርቶቮ ኮናሪ የተባለች መንደር ነው። የኢሬና እናት በወላጆችና መምህራን ስብሰባ ላይ ለኢሬና አስተማሪ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ሰጠቻት።

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አስተማሪዋ መጽሐፉን ይዛ በመምጣት ኢሬናን በክፍሏ ተማሪዎች ፊት እንድትቆም ጠየቀቻት። ከዚያም ለኢሬና እንዲህ አለቻት፦ “ዛሬ የምታስተምሪው አንቺ ነሽ። የመረጥኩትን ምዕራፍ ታነቢልናለሽ፤ በኋላም የእናንተ ቤተሰብ በምዕራፉ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ተግባራዊ የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ታብራሪልናለሽ።” አስተማሪዋ የመረጠችው “‘ወላጆቼን ማክበር’ የሚኖርብኝ ለምንድን ነው?” የሚለውን ምዕራፍ ነበር።

ኢሬና የተባለችውን ለማድረግ ወደፊት እየሄደች ሳለ አንዳንዶቹ ተማሪዎች የኢሬና ወላጆች የተለዩ እንደሆኑ ይናገሩ ጀመር። አስተማሪዋም ጣልቃ በመግባት እንዲህ አለቻቸው፦ “የእነሱ ቤተሰብ የተለየ የሆነው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስን ስለሚያጠኑ ነው። ታላላቅ ወንድሞቿን አስተምሬያቸዋለሁ፤ አስተማሪ ሆኜ ባሳለፍኳቸው ጊዜያት ሁሉ ሰው አክባሪ የሆኑና በምሳሌነት የሚጠቀስ አስተዳደግ ያላቸው እንዲህ ያሉ ልጆች አይቼ አላውቅም።”

ከዚያም አስተማሪዋ ኢሬና መጽሐፉን እንድታነብ ጠየቀቻት። ወላጆች ሕጎችን እንዲያወጡ አምላክ ኃላፊነት እንደሰጣቸው የሚናገረውን አንቀጽ ካነበበች በኋላ አስተማሪዋ “ኢሬና፣ የእናንተ ቤተሰብ ይህን ሐሳብ የሚሠራበት እንዴት ነው? ወላጆቻችሁ የሚሏችሁን ሁሉ እንደማይለወጥ ሕግ አድርጋችሁ ትመለከቱታላችሁ?” በማለት ጠየቀቻት።

ኢሬናም እንዲህ በማለት አብራራች፦ “እያንዳንዳችን የየራሳችን አመለካከት ይኖረን ይሆናል፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ወላጆቻቸውን ማክበርና መታዘዝ እንዳለባቸው ይናገራል፤ እኛም የምናደርገው ይህንኑ ነው። እንደዚያም ሆኖ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ተሰብስበን እንወያያለን፤ በዚህ ጊዜ እያንዳንዳችን ሐሳባችንን የመግለጽ አጋጣሚ እናገኛለን።” የትምህርት ክፍለ ጊዜው ሲያበቃ ኢሬና በሰጠችው ማብራሪያ ሁሉም ሰው ተደስቶ ነበር።

ይህ መጽሐፍ እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።