በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ውድ የሆነ ሀብት

ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ውድ የሆነ ሀብት

ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ውድ የሆነ ሀብት

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” (በአማርኛ አይገኝም) የተባለው ብሮሹር በእርግጥም ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ውድ ሀብት ሆኖላቸዋል። ይህ ብሮሹር ከ2,000 በሚበልጡ ዓመታት ውስጥ የተፈጸሙት ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች የተከናወኑባቸውን ቦታዎች የሚያሳዩ በርካታ ባለ ቀለም ካርታዎችንና ፎቶግራፎችን ይዟል። ከእነዚህ ፎቶዎች መካከል አብርሃም ይኖርባት የነበረውን የጥንቷን ቤርሳቤህ ፍርስራሽ እንዲሁም በመጀመሪያው መቶ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደተጓዙበት የሚታሰበውን በሮማውያን የተሠራ መንገድ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ይገኙበታል።

በርካታ አንባቢዎች ለብሮሹሩ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። አንዲት ሴት “የጥንቶቹ የእምነት አባቶች የኖሩባቸውን ቦታዎችም ሆነ ኢየሱስ የተጓዘበትን አካባቢ በዓይነ ሕሊናዬ ለመሳል እጓጓ ነበር” በማለት ጽፋለች። ሌላ ሴት ደግሞ “ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ ስመኘው የነበረ ነገር ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ላይ ሕይወት ይዘራባቸዋል” በማለት ተናግራለች።

ይህን ባለ 36 ገጽ ብሮሹር ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ። ይህ ብሮሹር በ79 ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ድረስ ወደ አሥር ሚሊዮን የሚጠጉ ቅጂዎች ታትመዋል።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የጥንቷ ቤርሳቤህ

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሮማውያን መንገድ

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Beer-sheba, Roman road, and brochure cover: Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.