በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘መተማመን መጥፋቱ ያስከተለው ቀውስ’

‘መተማመን መጥፋቱ ያስከተለው ቀውስ’

‘መተማመን መጥፋቱ ያስከተለው ቀውስ’

በምዕራብ አፍሪካ አንድ የ12 ዓመት ልጅ ታምሞ ሆስፒታል ተኝቷል፤ ልጁ የታመመው እናቱ ሕጋዊ ከሆነ አንድ የመድኃኒት መደብር የገዛችውን ተመሳስሎ የተሠራ ሐሰተኛ የወባ መድኃኒት በመውሰዱ ምክንያት ነው። አንድ ዶክተር “የሐሰት መድኃኒቶች በገበያ ላይ መታየት ከጀመሩ 15 ዓመታት ተቆጥረዋል” በማለት ተናግረዋል። *

በእስያ የሚኖሩ አንድ ባልና ሚስት፣ አራስ ልጃቸውን ሲያጠቡ የነበረው በአልሚ ምግቦች የበለጸገ ነው የተባለለት ወተት በአደገኛ ንጥረ ነገር የተበከለ መሆኑን ሲያውቁ በጣም ደነገጡ። የሚያሳዝነው፣ የሕፃኑን ሕይወት ማትረፍ አልተቻለም።

እምነት ይጣልበት የነበረ በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ አሜሪካዊ፣ ከደንበኞቹ ላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አጭበረበረ! በሺህ የሚቆጠሩት ደንበኞቹ፣ “የምዕተ ዓመቱ ታላቅ የማጭበርበር ተግባር” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ የማታለል ድርጊት ምክንያት ለጡረታ ሲከፍሉት የነበረው ገንዘብ እንደተወሰደ ደርሰውበታል።

ምንኖርበት ዓለም ውስጥ እምነት በጣለበት ሰው የማጭበርበር ድርጊት ያልተፈጸመበት ሰው የለም ማለት ይቻላል። ያለንበት ጊዜ መተማመን የጠፋበት ዘመን መሆኑ በመላው ዓለም ለተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ እንኳ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ለ ሞንድ የተባለው የፈረንሳይ ጋዜጣ ይህን ሁኔታ ‘መተማመን መጥፋቱ ያስከተለው ቀውስ’ በማለት ገልጾታል።

ባለንበት ጊዜ ‘መተማመን እንዲጠፋ’ ምክንያት የሆኑት ነገሮች ምንድን ናቸው? ልትተማመንበት የምትችለው አካል ይኖር ይሆን?

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.2 ፓሪስ፣ ፈረንሳይ ውስጥ የሚታተም ለ ፊጋሮ የተሰኘ ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ።