በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

ዘፍጥረት 4:1-8ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት፦

ቃየን፣ ይሖዋ የአቤልን መሥዋዕት ሲቀበል ምን ተሰማው? ወላጆችህ ለወንድምህ ወይም ለእህትህ የተለየ ነገር እንዳደረጉ ሲሰማህ ምን ማድረግ አይኖርብህም? ለምንስ?

ስለ ሐዋርያው ናትናኤል ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. የናትናኤል ሌላኛው ስሙ ማን ሊሆን ይችላል?

ፍንጭ፦ ሉቃስ 6:14ን እና ዮሐንስ 1:44-46ን አንብብ።

․․․․․

5. ኢየሱስ ያደነቀው የትኛውን የናትናኤልን ባሕርይ ነው?

ፍንጭ፦ ዮሐንስ 1:47ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

የናትናኤልን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረግህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል? ፍንጭ፦ መዝሙር 24:3-5ን እና 34:13-16ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 የሰው ልብ ወደ ምን ያዘነበለ ነው? ዘፍጥረት 8:․․․

ገጽ 6 ምን ዓይነት አኗኗር ለመኖር መመኘት ይኖርብናል? ዕብራውያን 13:․․․

ገጽ 24 ለወደፊቱ ጊዜ ምን ሊኖረን ይገባል? 1 ቆሮንቶስ 9:․․․

ገጽ 26 ነፋሱና አየሩ ጥሩ እስኪሆን ድረስ የምትጠባበቅ ከሆነ ምን ማድረግ አትችልም? መክብብ 11:․․․

● መልሶቹ በገጽ 21 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. መሥዋዕት ያቀረቡት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው።

2. ቃየን ያቀረበው የምድር ፍራፍሬዎችን ነው።

3. አቤል ያቀረበው ላም ሳይሆን በግ ነው።

4. በርቶሎሜዎስ።

5. ተንኮል የሌለበት መሆኑን።