በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሃሚንግበርድ ምላስ

የሃሚንግበርድ ምላስ

ንድፍ አውጪ አለው?

የሃሚንግበርድ ምላስ

ተመራማሪዎች መጠኑ በጣም አነስተኛ የሆነ የደም፣ የዲ ኤን ኤ ወይም የሌላ ንጥረ ነገር ናሙና የእጅህን መዳፍ በሚያህል መስተዋት ላይ አድርገው ይመረምራሉ። ተመራማሪዎቹ መጠናቸው በጣም አነስተኛ የሆኑ ነጠብጣቦችን ለማንቀሳቀስ በመምጠጫ ወይም በመንፊያ የሚጠቀሙ ቢሆንም እነዚህ ዘዴዎች የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ አይደሉም። በጣም ጥቃቅን የሆኑ ጠብታዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል የተሻለ ዘዴ ይኖር ይሆን? የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ጆን ቡሽ እንደተናገሩት “ተፈጥሮ ለዚህ ችግር መፍትሔ አለው።”

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሃሚንግበርድ የምትባለው ወፍ የአበቦችን ማር በመምጠጥ ጉልበቷን አታባክንም። ከዚህ ይልቅ ውኃ በጠፍጣፋ ነገር ላይ ሲያርፍ ጠብታዎች እንዲሠራ እንዲሁም ከስበት ሕግ በተቃራኒ እንዲሄድ በሚያደርገው ኃይል ትጠቀማለች። የሃሚንግበርድ ምላስ ከአበባው ማር ጋር በሚነካካበት ጊዜ ፈሳሹ ምላሷ እንዲጠቀለልና የአነስተኛ ቀሰም ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል፤ በዚህ ጊዜ የአበባው ማር ወፏ ሳትመጠው በራሱ ወደ ላይ ይወጣል። በሌላ አባባል ሃሚንግበርድ፣ የአበባው ማር እንደ ቀሰም በሆነው ምላሷ አልፎ በራሱ ሽቅብ በመውጣት ወደ አፏ እንዲገባ ስለምታደርግ የአበባውን ማር ለመምጠጥ ጉልበት አታባክንም። ሃሚንግበርዶች በሚመገቡበት ጊዜ በሴኮንድ እስከ 20 ጊዜ በሚደርስ ፍጥነት ምላሳቸውን በአበባ ማር መሙላት ይችላሉ!

ይህ ዓይነቱን ፈሳሽ ሽቅብ እንዲወጣ የማድረግ ዘዴ አንዳንድ የውኃ ዳር ወፎችም ውኃ ለመጠጣት ይጠቀሙበታል። በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኘው የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ማርክ ዴኒ ይህን ችሎታ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፦ “[በዚህ ዘዴ ላይ የሚታየው] የምሕንድስና፣ የፊዚክስና የሒሳብ ጥበብ ጥምረት በጣም አስደናቂ ነው። . . . ማንኛውንም መሐንዲስ ወይም የሒሳብ ሊቅ አንድ ወፍ በምንቃሩ ወደ ጉሮሮው ውኃ የሚያስገባበት ዘዴ ፈልግ ብትሉት ፈጽሞ ይህን ዘዴ ሊያስብ አይችልም።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ፈጣን በሆነና ጉልበት በማያባክን መንገድ የአበባ ማር የመሰብሰብ ችሎታ ያለው የሃሚንግበርድ ምላስ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Richard Mittleman/Gon2Foto/Alamy