በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አሁንም አዎንታዊ አመለካከት አለሽ”

“አሁንም አዎንታዊ አመለካከት አለሽ”

“አሁንም አዎንታዊ አመለካከት አለሽ”

ካሚላ የደም ማነስና የነርቭ ችግር ያለባት ከመሆኑም በላይ ሰውነቷ በተገቢው መንገድ አያድግም። በዚህም የተነሳ በስምንት ዓመቷ የነበራት ቁመት 75 ሴንቲ ሜትር ብቻ ነበር። በአርጀንቲና የሚኖሩትና የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑት የካሚላ ወላጆች በከተማቸው በሚገኝ አንድ የቲያትር አዳራሽ ውስጥ በሚካሄድ በሕክምና ዙሪያ የሚደረግ ስብሰባ ላይ ልጃቸውን ይዘው ለመገኘት ወሰኑ። እነሱም በአዳራሹ ሁለተኛ ረድፍ ላይ የተቀመጡ ሲሆን በስብሰባው ላይ 500 ሰዎች ተገኝተው ነበር።

አንድ ዶክተር ንግግር እየሰጠ ሳለ ካሚላን ሲመለከታት ጥሩ ጤንነት ያላት ስለመሰለው እሷን በምሳሌነት በመጥቀስ ወደ እሷ እያመለከተ መናገር ጀመረ። ስለ ልጅቷ ዕድሜም ሆነ የጤንነት ሁኔታ ምንም ስላላወቀ “ሕፃኗ ዕድሜዋ ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀ።

የካሚላ እናት ማሪሳ “ስምንት ዓመቷ ነው” በማለት መለሰችለት።

“ስምንት ወሯ ማለትሽ ነው?” በማለት ዶክተሩ በድጋሚ ጠየቃት።

ማሪሳም “አይደለም፣ ስምንት ዓመቷ ነው” በማለት አረጋገጠችለት።

ዶክተሩ ሁኔታውን ለማወቅ በጣም ስለጓጓ ለሚያቀርብላቸው አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡት እናቲቱንና ልጅቷን ወደ መድረክ እንዲወጡ ጋበዛቸው። ማሪሳ ዶክተሮች በካሚላ ላይ ያደረጉትን ጥናትና የሞከሩላትን ሕክምናዎች ከገለጸች በኋላ ዶክተሩ እንዲህ አለ፦ “ልጆቻቸው ጉንፋን ያዛቸው ብለው የሚያለቅሱ እናቶች አሉ። አንቺ ግን ካሚላን ሰባት ዓመት ካሳከምሽና የሚቻለውን ሁሉ ካደረግሽ በኋላ አሁንም አዎንታዊ አመለካከት አለሽ። ለመሆኑ እንዲህ ዓይነት አመለካከት ሊኖርሽ የቻለው እንዴት ነው?”

ማሪሳ በደግነት ለቀረበላት ለዚህ ጥያቄ መልስ ስትሰጥ የትኛውም ዓይነት በሽታና ሥቃይ አልፎ ተርፎም ሞት እንኳ ስለማይኖርበት ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ዓለም የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ለተሰብሳቢዎቹ ተናገረች። (ኢሳይያስ 33:24፤ ራእይ 21:3, 4) በመጨረሻም ማሪሳ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር ከገለጸች በኋላ የይሖዋ ምሥክሮች እርስ በርስ ያላቸው ፍቅር በሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን መከራዎችና ሌሎች ችግሮች ለመቋቋም እንዴት እንደሚረዳቸው አብራራች።—ዮሐንስ 13:35

ፕሮግራሙ ሲያበቃ አንዲት ሴት ወደ ማሪሳ ቀረብ ብላ ስለተናገረችው ነገር የበለጠ ማወቅ እንደምትፈልግ ገለጸችላት። ይህች ሴት የማወቅ ጉጉት ስላደረባት መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠና የቀረበላትን ግብዣ ተቀበለች፤ የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ቅዱሳን መጻሕፍትና አምላክ ለሰው ዘር ስላለው ድንቅ ዓላማ ለማወቅ ልባዊ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በነፃ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠናሉ።

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የስምንት ዓመቷ ካሚላ ከእናቷ ከማሪሳ ጋር