በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ማወቅ ያለብህ ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ማወቅ ያለብህ ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ማወቅ ያለብህ ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ዘመናት ሁሉ በሰፊው የተሰራጨ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ በጣም የሚወደድ መጽሐፍ ነው። ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ምሥክርነት ሲሰጡ የሚምሉበትና ለከፍተኛ ሥልጣን የተመረጡ ሰዎች እጃቸውን ጭነው ቃለ መሐላ የሚገቡበት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት አንድ ሰው ሊያገኘው ከሚችለው ማንኛውም ትምህርት ሁሉ እጅግ የላቀ ነው።

በርካታ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው ሕይወታቸውን በዚያ ቢመሩ ዓለም የተሻለች ስፍራ ትሆን እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተሰኘው ማራኪ ሥዕሎች ያሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹር መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር እንድታውቅ ሊረዳህ ይችላል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች ፈጣሪ ለሰዎች ገነትን ሰጥቶ እንደነበረና ሰዎች በዚያ የመኖር መብታቸውን እንዴት እንዳጡ ይገልጻሉ። ቀጣዮቹ ክፍሎች ደግሞ አምላክ በመንግሥቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሚሾመው ንጉሥ መገኛ ስለሆነው ሕዝብ የሚያወሳ ታሪካዊ ዘገባ ይዘዋል፤ በዚህ መንግሥት አማካኝነት ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች።

ቀጥሎ ያሉት ክፍሎች ደግሞ በአምላክ ስለተሾመው ገዥ ማለትም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት፣ አገልግሎት፣ ስለፈጸማቸው ተአምራት እንዲሁም ስለ ሞቱና ትንሣኤው ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ ያሉት አራት ክፍሎች በአንደኛው መቶ ዘመን የኖሩት የኢየሱስ ተከታዮች ስላከናወኑት አገልግሎት፣ በፈተና ወቅት ስላሳዩት እምነትና በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ስለጻፏቸው መጻሕፍት ይገልጻሉ። “ምድር ገነት ትሆናለች!” የሚለውን ክፍልና “የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት፣ አጠቃላይ ይዘት” የሚል ርዕስ ያለውን የሚያማምሩ ሥዕሎች የያዘውን የመጨረሻ ክፍል ማንበብህ እንደሚያበረታታህ እናምናለን።

ይህን ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።