በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ሳነበው አለቀስኩ”

“ሳነበው አለቀስኩ”

“ሳነበው አለቀስኩ”

እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ካነበበች በኋላ ከላይ ያለውን ሐሳብ የጻፈችው በኢሊኖይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት ሴት ናት። ይህች ሴት ለመጽሐፉ አዘጋጆች በጻፈችው ደብዳቤ ላይ “ብዙ ሰዎች ልክ እንደ እኔ ስለ ኢየሱስ ማንበብ እንደሚያስደስታቸው ተስፋ አደርጋለሁ፤ እንዲያነቡትም እጸልያለሁ” በማለት ተናግራለች።

ታላቅ ሰው የተባለው መጽሐፍ በኢየሱስ ዘመን የኖሩት ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ በመንፈስ ተመርተው በጻፏቸው ወንጌሎች ላይ ተመሥርቶ የኢየሱስን ሕይወት ይተርካል። ማቴዎስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩ የእሱ ሐዋርያት ናቸው። ማርቆስ የኢየሱስ ሐዋርያ የነበረው የጴጥሮስ የቅርብ ጓደኛ ነበር። ሐኪሙ ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያው ጳውሎስ የጉዞ ጓደኛ ነበር።

እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውን ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ