በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ያን ያህል ሕፃን አይደሉም

ያን ያህል ሕፃን አይደሉም

ያን ያህል ሕፃን አይደሉም

ከታላቁ አስተማሪ ተማር በተባለው መጽሐፍ ውስጥ የተብራራን አንድ ጉዳይ አስመልክታ ከላይ ያለውን አስተያየት የጻፈችው በካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት እናት ነበረች። ምክንያቷን ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “ባለፈው ሳምንት የ3 ዓመቱን ልጃችንን ጄቫንን ሐኪም ቤት ይዤው በሄድኩበት ጊዜ ዶክተሯ እኔና ባለቤቴ የፆታ ብልቶችን በተመለከተ ተገቢውን ትምህርት ለልጃችን አስተምረነው እንደሆነ ጠየቀችኝ። ማንም ቢሆን በሌላው ሰው የፆታ ብልት መጫወቱ ስህተት እንደሆነ ስለሚገልጸው ታላቁ አስተማሪ ስለተባለው መጽሐፍ ልነግራት በመቻሌ በጣም ደስ አለኝ። ዶክተሯም በዚህ ጉዳይ ላይ ከልጃችን ጋር እንደተወያየን ስታውቅ በጣም ገረማት።”

ይህች እናት “እነዚህ አስፈላጊ ጉዳዮች በመጽሐፉ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ተብራርተዋል” ብላለች። እሷ የጠቀሰችው ምዕራፍ “ኢየሱስ ጥበቃ ያገኘው እንዴት ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በሰማይ የሚኖረው የኢየሱስ አባት ልጁ ራሱን መጠበቅ በማይችልበት ዕድሜ ላይ ሳለ ክፉ ከሆነው ከንጉሥ ሄሮድስ የጠበቀው እንዴት እንደሆነ ያብራራል። (ማቴዎስ 2:7-23) ከዚያም መጽሐፉ ትንንሽ ልጆችም እንኳ በፆታ ሊያስነውራቸው ከሚሞክር ሰው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማስተማር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ይህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።