“አፍቃሪ የሆነውን አባት እንዳውቅ ስለረዳችሁኝ አመሰግናችኋለሁ”
“አፍቃሪ የሆነውን አባት እንዳውቅ ስለረዳችሁኝ አመሰግናችኋለሁ”
● በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት የ19 ዓመት ወጣት እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “አዘውትሮ ቤተ ክርስቲያን በሚሄድ ቤተሰብ ውስጥ ያደግሁ ሲሆን ክርስቶስንም እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁ። ያም ቢሆን አምላክ ሰዎችን አስፈሪ በሆነው ሲኦል ውስጥ በማቃጠል ይቀጣል ብዬ በማሰብ ለዓመታት በፍርሃት ስርድ ኖሬያለሁ። ከጊዜ በኋላ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፋችሁን አግኝቼ ማንበብ ጀመርኩ።
“ጥቂት ምዕራፎችን እንዳነበብኩ በውስጤ ይህ ነው የማይባል ሰላም ተሰማኝ። አንድ ትልቅ ሸክም ከላዬ የወረደ ያህል ቅልል አለኝ። አሁን ይሖዋ አፍቃሪ፣ ደግና መሐሪ አምላክ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ። ይሖዋ ከእሱ ጋር ዝምድና እንድመሠርት ቢፈልግም ይህን የማደርገው እሱን በመፍራት የተነሳ እንዲሆን አይሻም። የፊታችን እሁድ ወደ ይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ለመሄድ አስቤያለሁ! ሄጄ እስካየው በጣም ጓጉቻለሁ። እሳታማ ሲኦል ፈጥሯል የሚባለውን ሳይሆን አፍቃሪ የሆነውን አባት እንዳውቅ ስለረዳችሁኝ አመሰግናችኋለሁ።”
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮችንም ይዳስሳል። ከእነዚህ መካከል የሞቱ ሰዎች ስላሉበት ሁኔታ፣ ስለ ትንሣኤ ተስፋ፣ የቤተሰብን ሕይወት ማሻሻል ስለሚቻልበት መንገድ፣ ስለ አምላክና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እንዲሁም አምላክ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምን እንደሆነ የሚያብራሩት ርዕሶች ይገኙበታል። ይህ መጽሐፍ እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።