በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በጣም ከባድ ሐዘን

በጣም ከባድ ሐዘን

በጣም ከባድ ሐዘን

ኒኮል ጤናማ ልጅ ነበረች። አንድ ቀን አመሻሹ ላይ ራሷን እንዳመማት ስትናገር ወላጆቿ ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሄዱ። በማግስቱ ምሽት ላይ የሕክምና ክትትል እየተደረገላት ሳለ ኒኮል በልብ ሕመም ትሠቃይ ነበር። ተጨማሪ ምርመራዎች ሲደረጉላት ሳንባዋ፣ ኩላሊቷና ልቧ አልፎ አልፎ ብቻ በሚያጋጥም የባክቴሪያ ኢንፌክሽን እንደተጠቃ ታወቀ። የሚያሳዝነው በታመመች በ48 ሰዓት ውስጥ አረፈች። ኒኮል ስትሞት ገና የሦስት ዓመት ልጅ ነበረች።

የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት አንድ ሰው ሊደርስበት ከሚችለው አሳዛኝ ክስተት ሁሉ እጅግ የከፋው ነው። ግለሰቡ አንዳንድ ጊዜ ሐዘኑ ከአቅም በላይ እንደሆነ ሊሰማው ይችላል። የኒኮል እናት ኢዛቤል እንዲህ ብላለች፦ “ኒኮል በጣም ትናፍቀኛለች። ሁሌም እቅፍ ስታደርገኝ ይታየኛል፤ ጠረኗ እና የዋህነቷ ይናፍቀኛል። በየቀኑ አበባ ስትሰጠኝ የምታደርገው ነገር ትዝ ይለኛል። ኒኮል ምንጊዜም ከሐሳቤ አትጠፋም።”

አንተስ የምትወደውን ሰው ማለትም ልጅህን፣ የትዳር ጓደኛህን፣ ወንድምህን ወይም እህትህን፣ ወላጅህን ወይም የቅርብ ጓደኛህን በሞት ተነጥቀሃል? ከሆነ ሐዘኑን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?