በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?

ከ⁠አስቴር 5:9 እስከ 6:14⁠ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ትክክል ያልሆኑት ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት፦

ሐማ መርዶክዮስን የጠላው ለምን ነበር?

ፍንጭ፦ አስቴር 5:9⁠ን አንብብ።

ኩራት ሐማን ወደየትኛው የተሳሳተ መደምደሚያ እንዲደርስ አድርጎት ነበር?

ፍንጭ፦ አስቴር 6:6⁠ን አንብብ።

ሐማ ምን ደረሰበት?

ፍንጭ፦ አስቴር 7:9, 10⁠ን አንብብ።

እንደ ሐማ ዓይነት ሰው እንዳትሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 16:18, 19⁠ን እና ያዕቆብ 4:6⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

ከ⁠አስቴር 5:9 እስከ 6:14⁠ን በጋራ አንብቡ። የሚቻል ከሆነ አንደኛው ሰው ተራኪውን፣ ሁለተኛው ሰው ሐማን፣ ሦስተኛው ሰው ዞሳራንና የንጉሡን አገልጋዮች፣ አራተኛው ሰው ደግሞ ንጉሡን ወክሎ እንዲያነብ አድርጉ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 4 አስቴር

ጥያቄ

ሀ. አስቴር የተካችው የትኛዋን ንግሥት ነው?

ለ. መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ይህንን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “አስቴር በሚያዩዋት ሁሉ ዘንድ . . .”

ሐ. ክፍት ቦታዎቹን ሙላ። አስቴር በዕብራይስጥ የምትጠራበት ስም ________ ሲሆን ________ ለተባለው አሳዳጊዋ ደግሞ የአጎቱ ልጅ ነበረች።

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

አስቴር የኖረችበት ዘመን 400ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

አስቴር የሜዶ ፋርስ ግዛት ከተማ በሆነችው በሱሳ ኖራለች

ሜዶን

ሱሳ

ፋርስ

አስቴር

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የፋርሱ ንጉሥ ጠረክሲስ ሚስት ለመሆን የበቃች ወላጆቿ የሞቱባት ወጣት። አስቴር አይሁዳውያንን ለማጥፋት የተጠነሰሰውን ሴራ ለማክሸፍ ስትል ሕይወቷን ለአደጋ አጋልጣ ነበር። (አስቴር 4:11, 15, 16) ድፍረቷ፣ ብልሃቷና ታዛዥነቷ ከቁንጅናዋ ይልቅ ትልቅ ቦታ እንደሚሰጣቸው አስመሥክራለች።​—አስቴር 2:7፤ 1 ጴጥሮስ 3:1-5

መልስ

ሀ. አስጢንን።​—አስቴር 1:12፤ 2:16, 17

ለ. “. . . ሞገስ አገኘች።”​—አስቴር 2:15

ሐ. ሀደሳ (ባርሰነት ማለት ነው)፤ መርዶክዮስ።​—አስቴር 2:7

ሕዝቦችና አገሮች

4. ዩጂን እባላለሁ። የ7 ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በእስያ አህጉር በምትገኘው በኮሪያ ነው። በኮሪያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 9,700፤ 37,900 ወይስ 96,600?

5. የምኖርበትን አገር በሚጠቁመው ፊደል ላይ አክብብ። ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከኮሪያ ምን ያህል የሚርቅ ይመስልሃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● በገጽ 30 እና 31 ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች መልስ በገጽ 15 ላይ ይገኛል

በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. መርዶክዮስ መቀመጥ ያለበት ሠረገላ ላይ ሳይሆን የንጉሡ ፈረስ ላይ ነው።

2. መርዶክዮስ መልበስ ያለበት ተራ ካባ ሳይሆን የንጉሡን ልብሰ መንግሥት ነው።

3. መርዶክዮስ ማለፍ ያለበት በከተማው አደባባይ እንጂ ከከተማው ቅጥር ውጪ አይደለም።

4. 96,600።

5. መ።