በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ዘፍጥረት 13:5-17⁠ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

[ሠንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

በሎጥና በአብርሃም እንዲሁም በእረኞቻቸው መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ምን ነበር? አብርሃም የቤተሰብ ራስ እንደመሆኑ መጠን እርምጃ የመውሰድ መብት ቢኖረውም ሰላም ለመፍጠር ምን አደረገ?

ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 13:7-9⁠ን አንብብ።

ሎጥ የተሻለውን መሬት በመውሰዱ አብርሃም ተቀይሞት ይሆን?

ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 14:12-16⁠ን አንብብ።

አብርሃም አምላካዊ ባሕርይ ማንጸባረቁ ምን በረከት አስገኝቶለታል?

ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 13:14-17⁠ን አንብብ።

አንተስ ሰላም ፈጣሪ መሆንህን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 13:4, 5⁠ን እና ያዕቆብ 3:13-18⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

አንድ የቤተሰባችሁ አባል ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ያደረገውን ሁኔታ ምንም ድምፅ ሳይሰማ በእንቅስቃሴ ያሳይ። የቀሩት የቤተሰብ አባላት ደግሞ ማንን እያስመሰለ እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 5 አብርሃም

ጥያቄ

ሀ. አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ሲወለድ ስንት ዓመቱ ነበር?

ለ. ይሖዋ ለአብርሃም ምን እንደሚያደርግለት ቃል ገብቶለታል?

ሐ. ይህን ዓረፍተ ነገር አሟላ። አብርሃም ታላቅ እምነት ስለነበረውና ይህንንም በተግባር ስላሳየ ․․․․․. ተብሎ ለመጠራት በቅቷል።

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

አብርሃም የኖረበት ዘመን 1900ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከዑር ወደ ከነዓን ተጉዟል

ዑር

ካራን

ከነዓን

አብርሃም

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ይሖዋን በመታዘዝ የበለጸገችውን የዑር ከተማ ለቆ የወጣ ታማኝ የአምላክ አገልጋይ፤ በዚህ ወቅት የት ሊኖር እንደሚችል እንኳ አያውቅም ነበር። (ዕብራውያን 11:8-10) ‘ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የይሖዋን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ’ ዘወትር ቤተሰቡን ያስተምር ነበር። (ዘፍጥረት 18:19) መጽሐፍ ቅዱስ፣ አብርሃም “በእምነታቸው የተነሳ እንደ ጻድቃን ለተቆጠሩት ሁሉ አባት” እንደሆነ ይናገራል።​—ሮም 4:11

መልስ

ሀ. አንድ መቶ ዓመት።​—ዘፍጥረት 21:5

ለ. የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዘሩ አማካኝነት ይባረካሉ።​—ዘፍጥረት 22:16-18

ሐ. “የይሖዋ ወዳጅ።”​—ያዕቆብ 2:21-24

ሕዝቦችና አገሮች

3. ስማችን ራሄላ እና አንድሬ ይባላል። ሁለታችንም የሰባት ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በሩማንያ ነው። በሩማንያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 38,600, 68,300 ወይስ 83,600?

4. የምንኖርበትን አገር በሚጠቁመው ፊደል ላይ አክብብ። ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከሩማንያ ምን ያህል የሚርቅ ይመስልሃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 11 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ላም።

2. በግ።

3. 38,600።

4.