በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?

በሥዕል ሀ እና በሥዕል ለ መካከል ያሉትን ሦስት ልዩነቶች መናገር ትችላለህ? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

ፍንጭ፦ ዘፀአት 25:10-22⁠ን አንብብ።

1 ․․․․․

2 ․․․․․

3 ․․․․․

4. ትክክለኛው ሥዕል የትኛው ነው? ሥዕል ሀ ነው ወይስ ሥዕል ለ?

ለውይይት፦

በእስራኤላውያን ዘመን የቃል ኪዳኑ ታቦት ምንን ይወክል ነበር?

ፍንጭ፦ ዘፀአት 25:22⁠ን እና ዘሌዋውያን 16:2⁠ን አንብብ።

እስራኤላውያን ጥበቃ እንዲያገኙ ከታቦቱ መኖር ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምን ነበር?

ፍንጭ፦ ኢያሱ 7:1-6, 11, 12⁠ን አንብብ።

ወላጆችህንና ይሖዋን ማስደሰት ከፈለግህ ታዛዥ መሆንህ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 15:22, 23⁠ን እና ኤፌሶን 6:1-3⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዱ የቤተሰባችሁ አባል ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት ምርምር ያድርግ። ከዚያም አንድ ላይ ተሰብሰቡና ምን እንዳገኛችሁ ተነጋገሩ። ለምሳሌ ያህል፣ ከጊዜ በኋላ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ምን ነገሮች ተቀምጠዋል? እነዚህን ነገሮች በወረቀት ላይ ሳሏቸውና ምን ጥቅም እንደነበራቸው ተወያዩባቸው።

ፍንጭ፦ ዕብራውያን 9:4⁠ን አንብብ።

ታቦቱ መያዝ ያለበት እንዴት ነበር? ይሖዋ የታቦቱን አያያዝ አስመልክቶ የሰጠውን መመሪያ ዳዊት ባለማክበሩ ምክንያት ምን ተከሰተ?

ፍንጭ፦ ዘፀአት 37:5⁠ን፤ 1 ዜና መዋዕል 13:7, 9-14⁠ን እና 1 ዜና መዋዕል 15:12-15⁠ን አንብብ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 6 አቤል

ጥያቄ

ሀ. አቤልን የገደለው ማን ነው?

ለ. ይሖዋ አቤልንና ያቀረበውን መሥዋዕት የተመለከተው እንዴት ነው?

ሐ. ይህን ዓረፍተ ነገር አሟላ። የአቤል ሥራ ․․․․․ ነበር።

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

አቤል የኖረበት ዘመን 3900ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከኤደን ገነት ውጪ ኖሯል

ኤደን ገነት?

አቤል

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የአዳምና የሔዋን ሁለተኛ ልጅ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የእምነት ሰዎች ተብለው ከተጠሩት ሁሉ የመጀመሪያው ነው። አቤል በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት በማቅረብ የአምላክን ሞገስ ማግኘት እንደሚፈልግ አሳይቷል። ምንም እንኳ አቤል የተናገረው አንድም ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ባይገኝም እምነቱና የተወው ምሳሌ የእሱን ፈለግ እንድንከተል ያነሳሳናል።​—ዘፍጥረት 4:1-11፤ ዕብራውያን 11:4

መልስ

ሀ. ወንድሙ ቃየን።​—1 ዮሐንስ 3:11, 12

ለ. “በጥሩ ፊት።”​—ዘፍጥረት 4:4 NW

ሐ. የበግ እረኛ።​—ዘፍጥረት 4:2

ሕዝቦችና አገሮች

5. ዲን እና ጄኒፈር እንባላለን፤ የ10 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በአውስትራሊያ ነው። በአውስትራሊያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 36,400, 63,400 ወይስ 93,400?

6. የምንኖርበትን አገር በሚጠቁመው ፊደል ላይ አክብብ። ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከአውስትራሊያ ምን ያህል የሚርቅ ይመስልሃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 15 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. መሎጊያዎቹና ቀለበቶቹ የሉም።

2. የኪሩቦቹ ክንፎች በመክደኛው ላይ መዘርጋት ነበረባቸው።

3. ኪሩቦቹ ፊታቸውን ወደ መክደኛው መድፋት ነበረባቸው።

4. ለ።

5. 63,400።

6. ሐ።