ቤተሰብ የሚወያይበት
ቤተሰብ የሚወያይበት
በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተቶች ይታዩሃል?
የሐዋርያት ሥራ 9:36-41ን አንብብ። በዚህ ሥዕል ላይ ስህተት የሆኑት ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።
1. ․․․․․
2. ․․․․․
3. ․․․․․
ለውይይት፦
የጣቢታ ሌላኛው ስም ማን ነው? የስሞቿስ ትርጉም ምንድን ነው?
ፍንጭ፦ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ የሐዋርያት ሥራ 9:36ን የግርጌ ማስታወሻ አንብብ።
ጣቢታ ራስ ወዳድ ሴት ነበረች? አብራራ።
ፍንጭ፦ የሐዋርያት ሥራ 9:36, 39ን አንብብ።
ቢታ ሉቃስ 6:38 ላይ የሚገኘውን ኢየሱስ የተናገረውን ሐሳብ በሥራ ያዋለችው እንዴት ነው? የእሷን ምሳሌ መከተል የምትችለው እንዴት ነው?
ፍንጭ፦ ኤፌሶን 4:28ን እና ያዕቆብ 2:14-17ን አንብብ።
ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦
እያንዳንዱን የቤተሰብ አባላት ለማን ስጦታ መስጠት እንደሚፈልግ ተነጋገሩ። ከዚያም ለዚያ ሰው የሚሰጥ ቀለል ያለ ነገር አዘጋጁ። ለምሳሌ ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተጻፈበት ካርድ ወይም የመጽሐፍ ገጽ መለያ ምልክት መሥራት ትችላላችሁ።
ካርድ በመሰብሰብ መማር
ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው
የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 7 ጴጥሮስ
ጥያቄ
ሀ. ጴጥሮስ መስመጥ የጀመረው ለምንድን ነው?
ለ. ጴጥሮስ ጨርሶ ሚስት አላገባም። እውነት ወይስ ሐሰት?
ሐ. የሃይማኖት መሪዎቹ፣ መስበካቸውን እንዲያቆሙ ለሐዋርያቱ ሲነግሯቸው ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት እንዲህ የሚል መልስ ሰጥተዋል፦ “ከሰው ይልቅ . . . ”
[ሰንጠረዥ]
4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ
በመጀመሪያው መቶ ዘመን ኖረ
1 ዓ.ም.
98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ
[ካርታ]
በቤተሳይዳና በቅፍርናሆም ይኖር ነበር
ገሊላ
ቅፍርናሆም
ቤተሳይዳ
የገሊላ ባሕር
ጴጥሮስ
አጭር የሕይወት ታሪክ፦
ከመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ሲሆን ታታሪ የሆነ ዓሣ አጥማጅ ነበር። ኢየሱስ ጴጥሮስን ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት (የተላኩ ሰዎች ማለት ነው) መካከል እንዲሆን መርጦታል። አራቱ ወንጌሎች ላይ ከሌሎቹ ሐዋርያት ይበልጥ ጴጥሮስ የተናገራቸው ሐሳቦች ሰፍረው ይገኛሉ። ይሖዋ ለሌሎች ምሥራቹን እንዲያዳርስና ‘ወንድሞቹን እንዲያበረታ’ በብዙ መንገድ ተጠቅሞበታል።—ሉቃስ 22:32፤ ማርቆስ 3:13-19
መልስ
ሀ. ስለተጠራጠረ ነው።—ማቴዎስ 14:28-31
ለ. ሐሰት።—ማርቆስ 1:29-31፤ ዮሐንስ 1:42፤ 1 ቆሮንቶስ 9:5
ሐ. “. . . አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል።”—የሐዋርያት ሥራ 5:18, 27-29
ሕዝቦችና አገሮች
4. ስሜ አንቶንያ ይባላል። ዕድሜዬ ስምንት ዓመት ሲሆን የምኖረው በደቡብ አሜሪካ በምትገኘው በቺሊ ነው። በቺሊ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 69,500፣ 96,500 ወይስ 106,500?
5. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ። የምትኖርበት አገር ከቺሊ በጣም ይርቃል?
ሀ
ለ
ሐ
መ
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 23 ላይ ይገኛሉ
በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. ጴጥሮስ የጸለየው ቆሞ ሳይሆን ተንበርክኮ ነበር።
2. ሴቶቹ (መበለቶቹ) ለጴጥሮስ ያሳዩት ከሸክላ የተሠሩ ዕቃዎችን ሳይሆን ጣቢታ የሰፋቻቸውን ልብሶች ነው።
3. ጴጥሮስ የጸለየው ለብቻው ሆኖ ነበር፤ በክፍሉ ውስጥ ሌሎች ሰዎች ከእሱ ጋር አልነበሩም።
4. 69,500።
5. ለ።