በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

በላይኛው አማዞን የሚገኙ የተለያዩ አስደናቂ ፍጥረታት (ሚያዝያ 2010) ባወጣችሁት ጽሑፍ ላይ የአዋሁን ሕዝብ (አግዋሩና) አምስት አማልክትን እንደሚያመልኩ ገልጻችኋል። የአዋሁን ማኅበረሰብ ተወላጅ እንደመሆኔ መጠን በዚህ ሐሳብ አልስማማም። በዚህ ረገድ የተሳሳታችሁ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም አብዛኛው የአዋሁን ሕዝብ ክርስቲያን እንደሆነ የሚናገር ሲሆን በመጽሔታችሁም ላይ እንደተጠቀሰው አምስት አማልክት አናመልክም። የአዋሁን ማኅበረሰብ መጽሔታችሁን በብዛት ስለሚያነብ፣ እባካችሁ ይህን ስህተት አስተካክሉ።

ቲ. ፒ. ቲ.፣ ፔሩ

“የንቁ!” መጽሔት አዘጋጆች መልስ፦ የጽሑፉ አዘጋጅ የአግዋሩና ማኅበረሰብ የቀድሞ ነዋሪዎችን በግል ከማነጋገርና በርካታ ጽሑፎችን ከማመሳከር በተጨማሪ ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎችን አሰባስቧል። ከእነዚህ መካከል የ2004 እትም የሆነው “አትላስ ሪጅናል ደል ፔሩ” የተባለው መጽሐፍ አምስቱን የአግዋሩና አማልክት ስሞችና ስለ እነሱ የሚገልጹ ማብራሪያዎች ይዟል። ይሁን እንጂ እርሶ እንዳሉት አንዳንድ የአግዋሩና ማኅበረሰብ ነዋሪዎች ስመ ክርስትናን ተቀብለዋል። አንባቢዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ አድርገን ከሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን።

የመንተባተብን ችግር ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው? (ግንቦት 2010) በዚህ ርዕስ ሥር ለቀረበው ሐሳብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። እኔም የመንተባተብ ችግር አለብኝ፤ በዚህም የተነሳ ብዙውን ጊዜ ብቸኝነት ይሰማኛል። ይህን ርዕስ ካነበብኩ በኋላ ግን የችግሩ ተጠቂ እኔ ብቻ አለመሆኔን ተገንዝቤአለሁ። አሁን ያለብኝን ችግር ለመጋፈጥ ቆርጫለሁ፤ ደግሞም ልክ እንደ ራፋኤል ‘አንድ ቃል መጥራት አቅቶኝ በምንተባተብበት ጊዜ በራሴ እስቃለሁ’፤ በጉዳዩም ለመቀለድ እሞክራለሁ።

ዋይ. ኤስ.፣ ጃፓን

የወጣቶች ጥያቄ . . . ለራሴ ያለኝ ግምት ከፍ እንዲል ምን ላድርግ? (ግንቦት 2010) የ12 ዓመት ልጅ ነኝ፤ የምኖረው በጣም ታማሚ ከሆነችውና ብቻዋን ከምታሳድገኝ እናቴ ጋር ነው። “ሌሎች እንደሚወዱህ ይሰማሃል?” የሚለውን ጥያቄ ሳነብ “በፍጹም” ስል በሐቀኝነት መለስኩ። ይህ ደግሞ አበሳጨኝ። ስለሆነም ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከአንዳንድ ጎልማሳ ክርስቲያኖችና ከእናቴ ጋር ተነጋገርኩ። ይህ ርዕስ ራሴን ይህን ያህል የምኮንንበት ምንም ምክንያት እንደሌለ እንድገነዘብ ረድቶኛል። ብዙ ሰዎች እንደሚወዱኝ ማስተዋል ችያለሁ። ይሖዋ ለእኛ ለልጆች በጣም እንደሚያስብ መገንዘብ እንድችል ስለረዳችሁኝ አመሰግናችኋለሁ።

ኬ. ኤች.፣ ፈረንሳይ

ይህ ርዕስ ከዚህ በፊት ያጋጠሙኝን አሳዛኝ ሁኔታዎችና አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ የሚሰማኝን የከንቱነት ስሜት እንድቋቋም ረድቶኛል። በርዕሱ ውስጥ የተብራሩትን ለራሴ ያለኝን ግምት ከፍ ለማድረግ የሚረዱኝን ሦስት ዘዴዎች ፈጽሞ አልረሳቸውም! በተለይ ደግሞ ትንሽ ቀዳዳ ስላለው የብር ኖት የቀረበው ምሳሌ ልቤን በጥልቅ ነክቶታል። ለዚህ ግሩም ርዕሰ ትምህርት አመሰግናችኋለሁ!

ኤስ. ደብልዩ.፣ ደቡብ ኮሪያ