በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የንጉሥ ሰለሞን ጥበብ

የንጉሥ ሰለሞን ጥበብ

የንጉሥ ሰለሞን ጥበብ

● አንዲት መምህር የአራተኛ ክፍል ተማሪዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሰው ስለ ንጉሥ ሰለሞን የሚያውቁትን ነገር እንዲናገሩ ጠየቀቻቸው። የዘጠኝ ዓመቷ ሺና ሰለሞን የላቀ ጥበብ እንደነበረው ገለጸች፤ እንዲሁም ሁለት እናቶች አንድን ልጅ ‘የእኔ ልጅ ነው’ በማለት በተከራከሩ ጊዜ እንዴት አድርጎ መፍትሔ እንደሰጣቸው ተናገረች። የክፍሏ ተማሪዎች ሰለሞን ችግሩን የፈታበትን መንገድ ሲሰሙ መጀመሪያ ላይ ደንግጠው ነበር፤ ሆኖም መምህሯ ሰለሞን ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ትክክል እንደሆነ ገለጸች።

ሺና ይህን ታሪክ ልታውቅ የቻለችው ስለ ሰለሞን ጥበብ የሚናገረውንና ሌሎች ታሪኮችን የያዘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ በማንበቧ እንደሆነ ተናገረች። ሺና “አብረውኝ የሚማሩ ስድስት ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት ፈለጉ” በማለት ተናግራለች፤ አክላም “መምህሬም መጽሐፉን እንድሰጣት ጠየቀችኝ። በመሆኑም በአጠቃላይ ሰባት መጽሐፍ ማበርከት ችዬ ነበር” ብላለች።

እርስዎም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጹ ሰዎችና ክንውኖች የሚናገሩ 116 ታሪኮችን የያዘው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለው መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።