በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ ወዳጅ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

የአምላክ ወዳጅ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

የአምላክ ወዳጅ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ትምህርት ይሰጠናል። ብሮሹሩ ካሉት ማራኪ ርዕሶች መካከል “አምላክ ወዳጁ እንድትሆን ይጋብዝሃል” እና “አምላክ ከማንም የሚበልጥ ወዳጅ ነው” የሚሉት ይገኙበታል። ብሮሹሩ የተዘጋጀው አንባቢዎች መሠረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን እንዲገነዘቡ ለመርዳት ታስቦ ነው።

“የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ” የሚለው ርዕስ አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምን እንደሆነ በግልጽ ያብራራል። መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት ይመጣል ብሎ ተስፋ በሚሰጠው ገነት ውስጥ መኖር ከፈለግን፣ አምላክ እንድናገለግለው የሚፈልገው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። “እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ” እና “ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ!” እንደሚሉት ያሉ ርዕሶች የአምላክ ወዳጅ እንዲሆኑና የእሱን ሞገስ እንዲያገኙ ይረዱዎታል። ይህን ብሮሹር ሲያነቡ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያገኙ እርግጠኞች ነን።

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት አሊያም ይህ ብሮሹር እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።