በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ገጽ ሁለት

ገጽ ሁለት

ገጽ ሁለት

ልጆችን ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዲሆኑ አድርጎ ማሳደግ

አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች ጨቅላ ልጃቸውን ሲመለከቱ ጨርሶ ወደ አእምሯቸው የማይመጣ ቢሆንም የማይቀር ነገር አለ፦ በእቅፋቸው የያዙት ሕፃን የኋላ ኋላ ትልቅ ሰው ሆኖ ራሱን ችሎ መኖር ይጀምራል። ይህ የሕይወት እውነታ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ” እንደሚኖር ይገልጻል።—ዘፍጥረት 2:24

ይሁን እንጂ ልጆች አድገው ከቤት ሲወጡ ብዙ ወላጆች ደስታና ሐዘን የተቀላቀለበት ስሜት የሚያድርባቸው ከመሆኑም ሌላ ይጨነቃሉ። ‘ልጃችንን በተገቢው መንገድ አሳድገነዋል?’ ብለው ያስባሉ። ‘ልጃችን ሥራ ይዞ፣ የራሱ ቤት ኖሮት እንዲሁም የሚያገኘውን ገቢ አብቃቅቶ መኖር ይችል ይሆን?’ ከዚህም በላይ ‘ልጃችን ያስተማርነውን የሥነ ምግባር መሥፈርት ጠብቆ ይኖር ይሆን?’ የሚለው ጉዳይ ያሳስባቸዋል።—ምሳሌ 22:6፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:15

ይህ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም ልጆች ከሚያልፉበት ከእያንዳንዱ የእድገት ደረጃ ጋር በተያያዘ ወላጆች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋቸው ጥቅም የሚያስገኝላቸው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።