በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሚከተሉትን ሥዕሎች ከጥቅሶቹ ጋር አዛምድ

መክብብ 2:3-10⁠ን አንብብ። እያንዳንዱን ሥዕል ተስማሚ ከሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር አዛምድ። (ሥዕሎቹ የተቀመጡት ተዘበራርቀው ነው።) እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ቁጥር 3

2. ቁጥር 4

3. ቁጥር 5

4. ቁጥር 6

5. ቁጥር 7

6. ቁጥር 8

ለውይይት፦

ሰለሞን ባከናወናቸው ነገሮች እውነተኛ ደስታ ያገኘ ይመስልሃል?

ፍንጭ፦ መክብብ 2:11⁠ን አንብብ።

“ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል” ሲባል ምን ማለት ነው? እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምትችለው ምን ብታደርግ ነው?

ፍንጭ፦ ሉቃስ 6:38⁠ን እና የሐዋርያት ሥራ 20:35⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

መክብብ 3:1-8⁠ን አብራችሁ አንብቡ። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ነገሮች በተለያዩ የወረቀት ቁርጥራጮች ላይ እንዲጽፍ አድርጉ። ከዚያም ወረቀቶቹን አንድ ካርቶን ውስጥ ክተቷቸው። በኋላም እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ወረቀት መርጦ ያውጣና የተጻፈውን ነገር ያለ ንግግር በምልክት ብቻ ያሳይ። ከዚያም ቤተሰባችሁ ያንን ነገር በትክክል ለመገመት ይሞክር።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 11 ዮሴፍ

ጥያቄ

ሀ. ክፍት ቦታዎቹን ሙላ። የዮሴፍ ወንድሞች “ያ ․․․․․” ያሉት ሲሆን ወደ ባርነት የሸጡት በ ․․․․․ ጥሬ ብር ነበር።

ለ. የጲጥፋራ ሚስት አብሯት እንዲተኛ በገፋፋችው ጊዜ ዮሴፍ በቁርጠኝነት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ . . .”

ሐ. ፈርዖን ዮሴፍን በግብፅ ላይ ሁለተኛ ገዥ ያደረገው ለምንድን ነው?

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ዮሴፍ የኖረበት ዘመን 1700ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከዶታይን ወደ ግብፅ ተወሰደ

ዶታይን

ግብፅ

ዮሴፍ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የያዕቆብና የራሔል የመጀመሪያ ልጅ ነው። (ዘፍጥረት 35:24) ወንድሞቹ ስለቀኑበት በግብፅ ባሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ሸጡት፤ በዚያም ለ13 ዓመታት ባሪያ እንዲሁም እስረኛ ሆኖ ቆይቷል። ዮሴፍ ወንድሞቹን ከመበቀል ይልቅ ንስሐ ሲገቡ ይቅር ብሏቸዋል። (ዘፍጥረት 50:15-21) ከቤተሰቦቹ ርቆ የነበረ ቢሆንም ይሖዋን አስከብሯል፤ እንዲሁም በሥነ ምግባር ንጹሕ፣ ጠንካራ ሠራተኛና እምነት የሚጣልበት ሰው ሆኖ ኖሯል።​—ዘፍጥረት 39:1-23

መልስ

ሀ. ሕልም ዐላሚ፣ 20​—ዘፍጥረት 37:19, 28

ለ. “. . . እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት እሠራለሁ?”​—ዘፍጥረት 39:9

ሐ. የአምላክ መንፈስ ዮሴፍን ጥበበኛና አስተዋይ እንዳደረገው ስላወቀ ነው።​—ዘፍጥረት 41:38-41

ሕዝቦችና አገሮች

7. አኒቲ እባላለሁ። የሰባት ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በናይጄሪያ ነው። በናይጄሪያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 190,000፣ 290,000 ወይስ 390,000?

8. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከናይጄሪያ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.pr418.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 15 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. 1 እና ረ

2. 2 እና ሠ

3. 3 እና ሀ

4. 4 እና ሐ

5. 5 እና ለ

6. 6 እና መ

7. 290,000

8.