“ጥልቀት ያለው ደግሞም ለመረዳት ቀላል”
“ጥልቀት ያለው ደግሞም ለመረዳት ቀላል”
● ይህ በነብራስካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አንድ ሰው በቅርቡ ያነበቡትን መጽሐፍ አስመልክተው የሰጡት አስተያየት ነው። እኚህ ሰው እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “ዕድሜዬ 56 ዓመት ሲሆን ትዳር የለኝም፤ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ገና አንብቤ መጨረሴ ነው። መጽሐፉን አንብቤ እንደጨረስኩ ፍቅር በተንጸባረቀበት መንገድ የጻፋችሁት ይህ ትምህርት ምን ያህል ጥልቀት ያለው ደግሞም ለመረዳት ቀላል መሆኑን ማድነቅ ጀመርኩ።” አክለውም “ሥዕላዊ መግለጫዎቹ እጅግ በጣም ልዩ ናቸው ከማለት ውጪ ምንም ሊባል አይችልም። ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩኝ ኖሮ በመጽሐፉ ውስጥ የሰፈረውን ሐሳብ ብቻ ሳይሆን ሥዕሎቹንም ለእነሱ በማስረዳት ሰፋ ያለ ጊዜ የማሳልፍ ይመስለኛል” በማለት ጽፈዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በሆነችው በጆርጂያ የምትኖር አንዲት ሴትም ይህንኑ መጽሐፍ አስመልክታ እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ኤቭሪ የተባለችው የእህቴ ልጅ ስድስት ዓመቷ ሲሆን አብረዋት አንደኛ ክፍል ለሚማሩ ልጆች መጽሐፉን ለማሳየት ወደ ትምህርት ቤት ይዛው ትሄዳለች። ኤቭሪ ለክፍሏ ተማሪዎች አንድ ታሪክ ተናግራ ስታበቃ አስተማሪዋ በጣም ከመደነቋ የተነሳ ኤቭሪ በየቀኑ ከመጽሐፉ ላይ አንድ ታሪክ እንድታነብ ዝግጅት አደረገች።” የኤቭሪ አክስት አክላ እንዲህ ብላለች፦ “በእርግጥም ለክፍሏ ተማሪዎችም ሆነ ለአስተማሪዋ ስለ እምነቷ ትልቅ ምሥክርነት መስጠት ችላለች!”
እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ይህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሳምራዊው ጥሩ ባልንጀራ ነው የምንለው ለምንድን ነው?