በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ ላሳያቸው ፍቅር አድናቆት አላቸው

አምላክ ላሳያቸው ፍቅር አድናቆት አላቸው

አምላክ ላሳያቸው ፍቅር አድናቆት አላቸው

● ኢየሱስ አምላክ ላሳየን ፍቅር አድናቆት እንዲኖረን አስተምሮናል። እንዲህ ብሎ ነበር፦ “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።” (ዮሐንስ 3:16) ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለው መጽሐፍ አምላክ ለእኛ ስላለው ፍቅርና ልጁን በመስጠት ስለዘረጋልን አስደናቂ ተስፋ በስፋት ያብራራል።

በፍሎሪዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ምዕራፍ 5⁠ን ካነበብኩ በኋላ ይሖዋ ያለው ፍቅር፣ ጥበብና ታላቅ ኃይል በአድናቆት ስሜት እንድዋጥ አደረገኝ። ስለ ፍጥረት ሥራዎቹ ሳሰላስል ለእሱ ያለኝ ፍቅር ይበልጥ እየጨመረ ሄደ።” በሳውዝ ዳኮታ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ሌላ ሴት ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “ከ30 ለሚበልጡ ዓመታት ለሌሎች ፍቅር ማሳየት (ወይም የሚወደኝ ሰው እንዳለ ማሰብ) በጣም ፈታኝ ሆኖብኝ ነበር። ይህ መጽሐፍ ከሌሎች መጻሕፍት ማግኘት ያልቻልኩትን እርዳታ እየሰጠኝ ነው።”

ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለው ይህ ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ዋነኛ ስለሆኑት የአምላክ ባሕርያት ይኸውም ስለ ኃይሉ፣ ስለ ፍትሑ፣ ስለ ጥበቡና ስለ ፍቅሩ በስፋት ያብራራል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።