በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የወጣቶች ጥያቄ

መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት መደሰት የምችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት መደሰት የምችለው እንዴት ነው?

ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? እስቲ ይህን አስብ፦

መጽሐፍ ቅዱስ ውድ ሀብት እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል። ከማንኛውም ጽሑፍ ይበልጥ በብዛት የሚሸጠው ይህ መጽሐፍ

● ከሁሉ የተሻለ ሕይወት ለመምራት ያዘጋጅሃል

● ስላለፈው ዘመንም ሆነ ስለ ወደፊቱ ጊዜ በሌላ በምንም መንገድ ልታውቃቸው የማትችላቸውን ነገሮች ያሳውቅሃል

● ስለ ራስህ እንድታውቅና የተሻልክ ሰው እንድትሆን ይረዳሃል *

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም ይህን ማድረጉ መልሶ የሚክስ ነው! አንዳንድ ወጣቶች ይህን የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ? ቀጥሎ ያለውን ገጽ ቆርጠህ ካወጣኸው በኋላ ለሁለት እጠፈው። እኩዮችህ የሚያጋጥሟቸውን እንቅፋቶች ተቋቁመው መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው በማጥናት ጥቅም እያገኙ ያሉት እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ ቅልብጭ ያለ ሐሳብ በእነዚህ አራት ገጾች ላይ ታገኛለህ።

“መጽሐፍ ቅዱስ ለሁሉም ሰው የሚሆን ትምህርት ይዟል። በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስስ በመሆኑ መቼም ቢሆን የማጠናው ነገር ያልቅብኛል ብለህ አትሰጋም!”​ቫለሪ *

www.watchtower.org/ype በሚለው ድረ ገጽ ላይ “Young People Ask” በሚለው ዓምድ ሥር ተጨማሪ ርዕሶችን በእንግሊዝኛ ማግኘት ይቻላል።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.7 መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ሊያደርግልህ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ይበልጥ ለማወቅ በአቅራቢያህ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን ማነጋገር ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መጻፍ ትችላለህ።

^ አን.9 በዚህ ርዕስ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

[በገጽ 19 እና 20 ላይ የሚገኝ ሣጥን/​ሥዕል]

መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት​እንዴት?

ተፈታታኝ ሁኔታ፦ ፍላጎት ማጣት

“አንድ ሰዓት ሙሉ ቁጭ ብዬ የማጥናት ፍላጎት የለኝም።”​—ሊና

የሚያስፈልግህ፦ የሚያጓጓህ ነገር

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ አስደሳች እንዲሆንልህ ‘ከጥናቱ ምን ጥቅም አገኛለሁ?’ ብለህ ራስህን መጠየቅ ያስፈልግሃል። ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ትፈልጋለህ? በዓለም ላይ የሚከናወኑት ነገሮች ያላቸውን አንድምታ ይበልጥ መረዳት ትሻለህ? እንዲሁም ባሕርይህን ማሻሻል ትፈልጋለህ? መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህና ሌሎች ግቦች ላይ እንድትደርስ ሊረዳህ ይችላል!

“መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ሥራ እንደሆነ ወይም ከትምህርት ቤት ጥናት ጋር እንደሚመሳሰል አድርገህ አታስብ። ከዚህ ይልቅ ከሁሉ ከላቀው ወዳጅ ይኸውም ከይሖዋ አምላክ ጋር ለመቀራረብ የሚያስችል አጋጣሚ እንደሚከፍትልህ አድርገህ ተመልከተው።”​ቤተኒ

“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ከይሖዋ ጋር ብቻህን የምታሳልፈው ጊዜ ነው። ከአንድ ሰው ጋር ጊዜ የምታሳልፈው ወላጆችህ ሲኖሩ ብቻ ከሆነ ይህ ሰው የአንተ ጓደኛ ነው ወይስ የወላጆችህ? መጽሐፍ ቅዱስን በግልህ የምታጠና ከሆነ ይሖዋ የአንተ ወዳጅ ይሆናል።”​ቢያንካ

ይህን አስታውስ፦ “ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እንዲሁም ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ነገሮችን ለማቅናትና በጽድቅ ለመምከር ይጠቅማል።” (2 ጢሞቴዎስ 3:16) መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ መንገዶችም ሊረዳህ ይችላል!

“መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በሚያስገኛቸው ጥቅሞች ላይ ለማተኮር እጥራለሁ። በአንድ ነገር ላይ ማሻሻያ ማድረግ ካለብኝ የጥናት ፕሮግራሜ ይህን ለማድረግ የምችልባቸውን መንገዶች ለማወቅና ማሻሻያ ለማድረግ አጋጣሚ ይሰጠኛል።”​ማክስ

ልታስብበት የሚገባ ነጥብ፦

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚያጓጓህ ምንድን ነው?

ተፈታታኝ ሁኔታ፦ መሰላቸት

“ለ10 ደቂቃ ያህል ካጠናሁ በኋላ ይደካክመኛል፤ ከ20 ደቂቃ በኋላ ሌላ ነገር ብሠራ እመርጣለሁ፤ 30 ደቂቃ ሲሞላ ግን ትክት ይለኛል!”​—አሊሰን

የሚያስፈልግህ፦ የፈጠራ ችሎታ

ከምታጠናው ነገር፣ ከምታጠናበት መንገድ ወይም ቦታ ጋር በተያያዘ በየጊዜው አዲስ ነገር ለመፍጠር ሞክር።

“በአእምሮህ በሚፈጠሩ ጥያቄዎች ላይ ምርምር ለማድረግ ጊዜ መድብ። ጥያቄ ስላስነሳብህ ነገር ካጠናህ በኋላ እርካታ ይሰማሃል፤ አልፎ ተርፎም በጥናትህ ትደሰታለህ።”​ሪቻርድ

“አንድን ታሪክ ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። አንተ ራስህ ባለታሪኩ እንደሆንክ አድርገህ ለማሰብ ሞክር፤ አሊያም ደግሞ በቦታው ሆነህ ሁኔታውን እንደምትከታተል አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ሳለው።”​ስቲቨን

“ጥናትህን አስደሳች ለማድረግ ሞክር። የሚጠጣ ነገር ይዘህ ደጅ መቀመጥ ትችላለህ። በማጠናበት ጊዜ የምቀማምሰው ነገር ሲኖረኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው እንደዚህ የሚሰማው ይመስለኛል።”​አሊግዛንድራ

ይህን አስታውስ፦ መሰላቸት በአመለካከታችን ላይ የተመካ ነገር እንደሆነ አትርሳ። ስለዚህ “ጥናት አሰልቺ ነው” ከማለት ይልቅ “ማጥናት ሰልችቶኛል” ብትል ይሻላል። ለጥናት ያለህን አመለካከት ማስተካከል የአንተ ድርሻ እንደሆነ አስታውስ። ይህም ኃላፊነቱ የአንተ መሆኑን ተገንዝበህ ማሻሻያ እንድታደርግ ያነሳሳሃል።​—ምሳሌ 2:10, 11

“የግል ጥናት አሰልቺ መሆን የለበትም። ጥናትህን አስደሳች ልታደርገው ትችላለህ።”​ቨኔሳ

ልታስብበት የሚገባ ነጥብ፦

መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና የፈጠራ ችሎታህን መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?

ተፈታታኝ ሁኔታ፦ ጊዜ ማጣት

“መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ ባጠና ደስ ይለኛል፤ ሆኖም ፕሮግራሜ በጣም የተጣበበ ስለሆነ ጊዜ አግኝቼ ቁጭ ብዬ ማጥናት ለእኔ ትልቅ ፈተና ነው።”​—ማሪያ

የሚያስፈልግህ፦ ቅድሚያ መስጠት

ትልቅ ሰው መሆንህ ከሚታይባቸው መንገዶች አንዱ ‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይተህ ማወቅ’ መቻልህ ነው።​—ፊልጵስዩስ 1:10

“እናቴ ተጨማሪ ጊዜ ከየትም ማምጣት እንደማልችል እንድገነዘብ ረድታኛለች። ስለዚህ ጊዜዬን ማመቻቸት አለብኝ። የማጥናት ጉጉት ካዳበርኩ በኋላ ለጥናት የሚሆነኝ ጊዜ አመቻቸሁ።”​ናታንያ

“እያደግሁ ስሄድ ለጥናት ጊዜ መመደብ እንዳለብኝ ተምሬያለሁ። ምንም ነገር ቢያጋጥመኝ የጥናት ፕሮግራሜን አከብራለሁ።”​ዮላንዳ

“ከመዝናኛ በፊት ጥናትን የምታስቀድም ከሆነ ጥናትህ ይበልጥ አስደሳች እንደሚሆንልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ከዚያ በኋላ ስትዝናና የጥፋተኝነት ስሜት አይኖርህም።”​ዳያና

ይህን አስታውስ፦ ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ የማትሰጥ ከሆነ ጊዜህን በአግባቡ መጠቀም አትችልም፤ መቼም ቢሆን አይሞላልህም። ከዚህ ይልቅ ለጥናትህ ቅድሚያ በመስጠት ጊዜ መመደብህ በጣም የተሻለ ነው።​—ኤፌሶን 5:15, 16

“የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እንደመሆኔ መጠን ጊዜዬን የሚሻሙብኝ ብዙ ነገሮች አሉ! ሆኖም ፕሮግራም ሳወጣ ለግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቴ ቅድሚያ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።”​ጆርዳን

ልታስብበት የሚገባ ነጥብ፦

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ምን ዓይነት ፕሮግራም ማውጣት ትችላለህ?

[በገጽ 19 ላይ የሚገኝ ሣጥን/​ሥዕል]

እኩዮችህ የሰጧቸው ጠቃሚ ሐሳቦች

ዛከሪ​—አንድን ርዕሰ ጉዳይ ወላጆችህ ወይም ሌሎች ሰዎች ስላጠኑት ብቻ ልታጠናው አይገባም። የግል ጥናት የሚባለው አንተ ምርምር ልታደርግበት የምትፈልግ ርዕስ ከሆነ ነው።

ካሊ​—መጀመሪያ ላይ የግድ ለረጅም ሰዓት ማጥናት አያስፈልግህም። በየቀኑ አድርገው እንጂ አምስት ደቂቃም በቂ ሊሆን ይችላል። ከዚያም 10 ደቂቃ፣ 15 ደቂቃ . . . እያልክ የምታጠናበትን ጊዜ ልታስረዝመው ትችላለህ። ብዙም ሳይቆይ ጥናቱን እየወደድከው ትሄዳለህ!

ዳንዬላ​—ትንንሽ ነገሮች እንኳ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። የተለያየ ቀለም ያላቸው እስክሪቢቶዎችን ተጠቀም እንዲሁም ቆንጆ የማስታወሻ ደብተር ይኑርህ፤ ወይም ደግሞ በኮምፒውተርህ ላይ ‘የግል ጥናት’ የሚል ፋይል አዘጋጅ።

ጆርዳን​—የምወደውን ርዕስ ከመረጥኩ ረዘም ያለ ሰዓት ማጥናት እችላለሁ። ማጥናት የምፈልገው ደግሞ ጸጥ ባለ አካባቢ ነው። የሚረብሹኝ ድምፆች ካሉ ማጥናት ያስቸግረኛል።

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ቁረጠው

እጠፈው