በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ስለ ዓይን የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር

ስለ ዓይን የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር

ስለ ዓይን የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር

● የሰው ልጆች ዓይን በጣም አስገራሚ ውበት ብቻ ሳይሆን ልዩ የሆነ ችሎታም አለው። ማየት ያለው ኃይል፣ በማየት የሚገኝ ትምህርት (እንግሊዝኛ) የተሰኘው መጽሐፍ “ከአንጎል ጋር ከተገናኙት ነርቮች መካከል አርባ በመቶ የሚያህሉት ከሬቲና ጋር የተያያዙ ናቸው” ይላል፤ ሬቲና በውስጠኛው የዓይናችን ክፍል የሚገኝ ስስ ሆኖም ውስብስብ የሆነ ኅብረ ሕዋስ ነው።

በእርግጥም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓይንን “የሰውነት መብራት” በማለት መጥራቱ ተገቢ ነው። ኢየሱስ ይህን ሐሳብ ሲያብራራ “ዓይንህ አጥርቶ የሚያይ [በመልካም ነገር ላይ ያተኮረ] ከሆነ መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል። ይሁን እንጂ ዓይንህ የሚቅበዘበዝ ከሆነ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል” ብሏል። (ማቴዎስ 6:22, 23) ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ ዓይን ያለውን ኃይል ይኸውም በዓይናችን የምናየው ነገር በሐሳባችን፣ በስሜታችን እንዲሁም በድርጊታችን ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በምሳሌያዊ መንገድ ጎላ አድርጎ ገልጿል። ጥሩ ሐሳቦች የአንድን ሰው ሕይወት ብሩህ የሚያደርጉለት ሲሆን ክፉ ሐሳቦች ደግሞ ሕይወቱን ያጨልሙበታል።

ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ በ⁠ማቴዎስ 5:28, 29 ላይ የተናገረውን የሚከተለውን ሐሳብ ልብ በል፦ “የፆታ ስሜቱ እስኪቀሰቀስ ድረስ አንዲትን ሴት በምኞት የሚመለከት ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል። ስለዚህ ቀኝ ዓይንህ ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው።” ኢየሱስ እዚህ ላይ ሊያስተላልፍ የፈለገው ፍሬ ነገር ምንድን ነው? እርግጥ ነው፣ ቃል በቃል ዓይናችንን ማውጣት እንዳለብን መግለጹ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ የሚቅበዘበዝ ዓይን፣ አንድ ግለሰብ መጥፎ ምኞቶች እንዲቀሰቀሱበት ሊያደርግና አጋጣሚውን ቢያገኝ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ድርጊት እንዲፈጽም ሊያነሳሳው እንደሚችል መግለጹ ነው፤ ግለሰቡ እንዲህ ማድረጉ ደግሞ የአምላክን ሞገስ ያሳጣዋል።​—ያዕቆብ 1:14, 15

ራስን መግዛት ዓይንን አውጥቶ የመጣል ያህል ከባድ ቢሆንም እንኳ እንዲህ ማድረጉ ምንኛ የተሻለ ነው! ደግሞስ ቅጽበታዊ ለሆነ ደስታ ብሎ የዘላለም ሕይወትን መሥዋዕት ማድረግ ጥበብ ነው?

በተጨማሪም በዓይናችን የሚገባው ነገር በውስጣችን የስግብግብነትን ዘር ሊዘራ ይችላል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ራስ ወዳድነትን የሚያንጸባርቅ “የዓይን አምሮት . . . ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመነጭ” እንዳልሆነ ይናገራል፤ “ከዚህም በተጨማሪ ዓለምም ሆነ ምኞቱ በማለፍ ላይ ናቸው፤ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል” በማለት ያስጠነቅቀናል።​—1 ዮሐንስ 2:16, 17

ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው ይህ ማስጠንቀቂያ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ነው? በጭራሽ! እንዲያውም የመጽሐፍ ቅዱስን መሥፈርቶች ችላ ማለት በራሳችን ላይ ችግርንና ሐዘንን መጋበዝ ነው። (ገላትያ 6:7, 8) በሌላ በኩል ግን መጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊውን ዓይናችንን ስለምንጠቀምበት መንገድ የሚሰጠውን ጥበብ ያዘለ ምክር ጨምሮ የአምላክ ቃል የሚናገረውን ሰምተን ተግባራዊ ማድረጋችን ደስታን ለማጨድ ያስችለናል። ኢየሱስ ‘የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁ ደስተኞች’ እንደሆኑ ተናግሯል። (ሉቃስ 11:28) ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ሕይወት የሚመሩ ወይም ስግብግብ ዓይን ያላቸው ሰዎች ደስታም ሆነ የዘላለም ሕይወት የሚያጡ ሲሆን የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ግን በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ አላቸው።