በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በእርስዎ አመለካከት ኢየሱስ . . .

በእርስዎ አመለካከት ኢየሱስ . . .

በእርስዎ አመለካከት ኢየሱስ . . .

አራስ ሕፃን ነው? ሞት አፋፍ ላይ ያለ ሰው ነው? ወይስ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢየሱስ ኃያል ንጉሥ እንደሆነ ይናገራል። ታዲያ ይህ ለእርስዎ ምን ትርጉም አለው?

ብዙ ሰዎች ኢየሱስ እንደሞተላቸው ያምናሉ። ሆኖም አንድ ሰው ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት መሞቱ በዛሬው ጊዜ ለሚኖሩ ሰዎች መዳን የሚያስገኘው እንዴት ነው?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ እንዲያዳምጡ በአክብሮት ተጋብዘዋል። ይህ ሐሳብ የሚብራራው የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ በሚያከብሩበት ዕለት ነው። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው ሐሙስ፣ መጋቢት 27, 2004 (April 5, 2012) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው።

ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክዎ በአካባቢዎ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ያነጋግሩ።