በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?

በሥዕል ሀ እና ለ መካከል ያሉትን ሦስት ልዩነቶች መናገር ትችላለህ? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 16:1-3, 6-13⁠ን አንብብ።

1 ․․․․․

2 ․․․․․

3 ․․․․․

4. ትክክለኛው ሥዕል የትኛው ነው? ሥዕል ሀ ወይስ ሥዕል ለ?

ለውይይት፦

ይሖዋ አንድን ሰው ሲያይ የሚመለከተው ምኑን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ “ልብን ያያል” ሲል ምን ማለቱ ነው?

ፍንጭ፦ ኤርምያስ 17:10⁠ን አንብብ።

ይሖዋ፣ ለውጫዊ ገጽታ ምን ያህል ቦታ ይሰጣል?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 11:22⁠ን፤ ምሳሌ 31:30⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 3:3, 4⁠ን አንብብ።

በአምላክ ፊት ውብ ሆነህ እንድትታይ የሚያደርጉህ ባሕርያት የትኞቹ ናቸው?

ፍንጭ፦ ሉቃስ 10:27⁠ን እና 2 ጴጥሮስ 1:5-8⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

ገላትያ 5:22, 23⁠ን አንብብ። ዘጠኙን ባሕርያት በተለያየ ወረቀት ላይ ጻፋቸው። አንድ የቤተሰብህን አባል ምረጥና አንዱን ባሕርይ የጻፍክበትን ወረቀት በፕላስተር ጀርባው ላይ ለጥፈው። ለግለሰቡ ጀርባው ላይ የሚለጠፈው ባሕርይ ምን እንደሆነ አታሳየው። ግለሰቡ ይህን ባሕርይ ለማወቅ የቤተሰቡን አባላት ጥያቄዎች እንዲጠይቅ አድርግ። የተቀሩት የቤተሰብ አባላት ‘አዎ’ ወይም ‘አይደለም’ የሚል መልስ ብቻ ይሰጡታል።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 15 ዳዊት

ጥያቄ

ሀ. ዳዊትም ሆነ ኢየሱስ የተወለዱት በየትኛዋ ከተማ ነው?

ለ. ዳዊት ልጅ እያለ ․․․․․ የነበረ ሲሆን ․․․․․ እና ․․․․․ በድፍረት ገድሏል።

ሐ. ዳዊት የተናገረውን የሚከተለውን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ . . .”

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

1000 ዓ.ዓ. ገደማ ዳዊት የኖረበት ዘመን

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

ከቤተልሔም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ

ቤተልሔም

ኢየሩሳሌም

በዔላ ሸለቆ ከጎልያድ ጋር ተዋጋ።​—1 ሳሙኤል 17:2

የዔላ ሸለቆ

ዳዊት

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የእሴይ ልጅ፣ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ። የተካነ ገጣሚና ሙዚቀኛ የሆነው ዳዊት ከ73 የሚበልጡ መዝሙሮችን ጽፏል። በሕይወቱ ውስጥ የይሖዋን አመራር ለማግኘት በትሕትና ፈልጓል። (1 ሳሙኤል 23:2፤ 30:8፤ 2 ሳሙኤል 2:1) ይሖዋ ዳዊትን “እንደ ልቤ የሆነው” በማለት ጠርቶታል።​—የሐዋርያት ሥራ 13:22

መልስ

ሀ. በቤተልሔም (በይሁዳ በምትገኘው)።​—ዮሐንስ 7:42

ለ. እረኛ፣ አንበሳ፣ ድብ።​—1 ሳሙኤል 17:34, 35፤ መዝሙር 78:70, 71

ሐ. “. . . እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው።”​—1 ዜና መዋዕል 28:9

ሕዝቦችና አገሮች

5. ኦሊቪያ እባላለሁ፤ የስድስት ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በኢንዶኔዥያ ነው። በኢንዶኔዥያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 22,300፣ 42,800 ወይስ 63,900?

6. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከኢንዶኔዥያ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.pr418.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 22 ላይ ይገኛሉ

[በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. በአንደኛው ሥዕል ላይ ያለው ፍየል ሲሆን በሁለተኛው ሥዕል ላይ የምትታየው ግን ጊደር ናት

2. በአንደኛው ሥዕል ላይ ሴት ልጅ ያለች ሲሆን በሌላኛው ላይ ግን የለችም

3. በአንደኛው ሥዕል ላይ የሚታየው የወይን አቁማዳ ሲሆን በሌላኛው ሥዕል ላይ የሚታየው ግን በዘይት የተሞላ ቀንድ ነው

4. 

5. 22,300

6.