የወጣቶች ጥያቄ
ተወዳጅ መሆን ስህተት ነው?
ባዶ ቦታውን ሙላ።
ተወዳጅ መሆን ․․․․․
-
ሀ. ሁልጊዜ ጥሩ ነው
-
ለ. አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ነው
-
ሐ. ፈጽሞ ጥሩ አይደለም
ትክክለኛው መልስ “ለ” ነው። ለምን? ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ መሆን ሲባል ተቀባይነት ማግኘት ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ስህተት አይደለም! መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች “የአሕዛብ ብርሃን” እንደሚሆኑና ሕዝቦች ወደ እነሱ እንደሚሳቡ ትንቢት ተናግሯል። (ኢሳይያስ 42:6፤ የሐዋርያት ሥራ 13:47) ከዚህ አንጻር ሲታይ ክርስቲያኖች ተወዳጅ ናቸው ማለት ይቻላል።
ይህን ታውቅ ነበር?
ተወዳጅነት ማትረፉ ስህተት ነበር?
አልነበረም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክብር ወይም ተወዳጅነት ለማትረፍ የሚፈልግ ሰው አይደለም፤ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘትም የተለየ ጥረት አላደረገም። ኢየሱስ ትክክል የሆነውን ከመፈጸም ውጪ ያደረገው ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን ሞገስ ለማግኘት አስችሎታል። (ዮሐንስ 8:29, 30) በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ፣ የሕዝቡ አቋም ተለዋዋጭ እንደሆነ ስለሚያውቅ በእነሱ ዘንድ ያተረፈው ተወዳጅነት ጊዜያዊ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። እንዲያውም ይህ ሕዝብ ከጊዜ በኋላ እንደሚያስገድለው ተናግሯል!—ሉቃስ 9:22
ዋናው ነጥብ፦
ተወዳጅነት ማትረፍ ሀብት እንደ ማግኘት ነው። ሀብት ማግኘት አብዛኛውን ጊዜ ስህተት አይደለም። ችግሩ ያለው ሰዎች ሀብት ለማግኘት ወይም ያገኙትን ሀብት ላለማጣት ሲሉ በሚወስዱት እርምጃ ላይ ነው።
ማስጠንቀቂያ!
ብዙ ወጣቶች ተወዳጅነት ለማትረፍ ሲሉ የማያደርጉት ነገር የለም። አንዳንዶቹ ሰው ያደረገውን የሚያደርጉ ልወደድ ባዮች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ሰዎችን በማስፈራራት ተቀባይነት ለማትረፍ የሚጥሩ ጉልበተኞች ናቸው። *
በቀጣዮቹ ገጾች ላይ ሰዎች ተወዳጅነት ለማትረፍ የሚከተሏቸውን እነዚህን ሁለት የተሳሳቱ ጎዳናዎች እንመለከታለን። ከዚያም የተሻለውን መንገድ እንመረምራለን።